ዊንድሁክ

ቪንድሁክ (Windhoek)ናሚቢያ ዋና ከተማ ናት። የሚኖርበት ሕዝብ በዛቷ 221,000 - 230,000 ሆኖ ይገመታል። ከተማዋ ዋና የበግ ቆዳ መሸጫ ማዕከል ናት።

ዊንድሁክ
ዊንድሁክ

ሄሬሮ ጎሣ የሥፍራው መጀመርያ ኗሪዎች ሲሆኑ በቋንቋቸው ኦቾሞይዝ ተባለ። ከዚያ የናማ ሕዝብ ቦታውን አይጋምስ አሉት። የአሁኑ ከተማ በ1883 ዓ.ም. በጀርመኖች ተሠራ።

የከተማዋ ከንቲቫ አሁን (በ1999 ዓ.ም.) ማቲውስ ሺኮንጎ ነው። ከተማው 22°34′ ደቡብ ኬክሮስ እና 17°06′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.