ኖቤል ሽልማት

የኖቤል ሽልማቶች ከ1893 ዓም ጀምሮ በስዊድን ሳይንቲስት አልፍሬድ ኖቤል ስም በየዓመቱ የሚሰጡ ታላቅ ስልማቶች ናቸው። አልፍሬድ ኖቤል በኑዛዜው በገዛ ሀብቱ የሽልማቱን ሥርዓት መሠረተ። ሽልማቶቹ በሚከተሉት መደቦች ይሠጣሉ።

  • የኖቤል ሽልማት በፊዚክስ
  • የኖቤል ሽልማት በኬሚስትሪ
  • የኖቤል ሽልማት በሕክምና
  • የኖቤል ሽልማት በሥነ ጽሑፍ
  • (ከ1961 ዓም ጀምሮ) የኖቤል ሽልማት በምጣኔ ሀብት (በይፋ «የስዊድን ባንክ ሽልማት በምጣኔ ሀብት» ይባላል)
  • የኖቤል ሰላም ሽልማት
አንድ የኖቤል ሽልማት

የኖቤል ሰላም ሽልማትኖርዌይ ምክር ቤት ጉባኤ ይወሰናል። ሌሎቹ ሽልማቶቹ በስዊድን ተቋማት ይወሰናሉ።

ከወርቃማው ሽልማት በላይ ተቀባዮች አንድ ሚሊዮን ዶላር ያህል ያገኛሉ።

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.