ሴይንት ህሊና፣ አሰንሽንና ትሪስተን ደ ኩና
ሴይንት ህሊና፣ አሰንሽንና ትሪስተን ደ ኩና (እንግሊዝኛ፦ Saint Helena, Ascension and Tristan da Cunha) በአትላንቲክ ውቅያኖስ የሚገኝ የእንግሊዝ ቅኝ (ጥገኛ) አገር ነው። ሴይንት ህሊና ደሴት፣ አሰንሽን ደሴት እና ትሪስተን ደ ኩና ያጠቅልላል።

የሴይንት ህሊና፣ አሰንሽንና ትሪስተን ደ ኩና ሥፍራዎች
ከነሐሴ 26 ቀን 2001 ዓ.ም. በፊት፣ አሰንሸን ደሴት እና ትሪስተን ደ ኩና በሴይንት ህሊና ጥገኝነት ሥር ኖረው ነበር፤ በዚያ ቀን ግን ሦስቱ ግዛቶች በሕግ እኩል ተደርገው የጠቅላላ ግዛቱ ይፋዊ ስም ከ«ሴይንት ህሊናና ጥገኞቿ» ወደ «ሴይንት ህሊና፣ አሰንሽንና ትሪስተን ደ ኩና» ተቀየረ።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.