ሬዩንዮን
ሬዩንዮን በሕንድ ውቅያኖስ የተገኘ የፈረንሳይ ቅኝ (ጥገኛ) አገር ደሴት ነው። 802,000 ያሕል ሰዎች ይኖሩበታል።

ሬዩንዮን
ደሴቱ ለአረብ መርከበኞች «አድና አል ማግሪባይን» በመባል ይታወቅ ነበር። ፖርቱጊዝ በ1627 አ.ም. ያለ ምንም ኗሪ አገኝተውት «ሳንታ አፖሎኒያ» አሉት። ፈረንሳይ በ1634 ዓ.ም. ያዙትና በ1641 ዓ.ም. «ኢል ቦርቦን» አሉት። በ1785 ዓ.ም. ስሙ «ሬዩንዮን» ሆነ። ከ1793 ዓ.ም. እስከ 1802 ዓ.ም. ድረስ ግን ስሙ «ኢል ቦናፓርት» ከዚያም እስከ 1840 ዓ.ም. ድረስ እንደገና «ቦርቦን» ይባል ነበር። ከ1840 ዓ.ም. እስካሁን «ሬዩንዮን» ተብሏል።

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.