Z

Z / zላቲን አልፋቤት 26ኛ እና መጨረሻው ፊደል ነው።

ግብፅኛ
መር
ቅድመ ሴማዊ
ዛይን
የፊንቄ ጽሕፈት
ዛይን
የግሪክ ጽሕፈት
ዜታ
ኤትሩስካዊ
Z
ላቲን
Z
U7
Greek nu Roman N
የላቲን አልፋቤት
ABCDEF
GHIJKLM
NOPQRST
UVWXYZ
ተጨማሪ ምልክቶች፦
Þ...

የ«Z» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ዛይን» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የመኮትኮቻ ስዕል መሰለ። ለዚህ ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ፣ ከዚህም በግሪክ አልፋቤት "ዜታ" (Ζ ζ) ደረሰ።

በነዚህ አልፋቤቶች ሁሉ እንዲሁም በጥንታዊ ኢታሊክ አልፋቤት፣ ይህ ፊደል 𐌆 (Z ወኡም /ዝ/) ሰባተኛው ነበር። በሮማይስጥ ግን፣ በአንዳንድ መዝገቦች ዘንድ፣ የሮሜ ኬንሶርና አምባገነን አፒዩስ ክላውዲዩስ ካይኩስ በ320 ዓክልበ. «Z»ን ስላልወደደ ከላቲን ፊደል እንደ ጣለው ይባላል።

ሆኖም የ/ዝ/ ድምጽ በግሪክኛ ስለተገኘ፣ በጊዜ ላይ የግሪክ ወይም የሌሎችም ቋንቋዎች ቃላት በሮማይስጥ ለመጻፍ የ/ዝ/ ምልክት አስፈላጊነት እንደገና ታየ። ስለዚህ ከ85 ዓም ግድም በኋላ የግሪኩ ቅርጽ Z እንደገና ለዚህ ድምጽ ወደ ሮማይስጥ ተበደረ። በቀድሞው ሰባተኛው ሥፍራ አዲሱ ፊደል G ተሳክቶ ስለ ሆነ፣ Z አሁን መጨረሻውን ቦታ ወሰደ።

ግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «ዘ» («ዘይ») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ዛይን» ስለ መጣ፣ የላቲን 'Z' ዘመድ ሊባል ይችላል።

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.