W
W / w በላቲን አልፋቤት 23ኛው ፊደል ነው።
የላቲን አልፋቤት | ||||||
---|---|---|---|---|---|---|
A | B | C | D | E | F | |
G | H | I | J | K | L | M |
N | O | P | Q | R | S | T |
U | V | W | X | Y | Z | |
ተጨማሪ ምልክቶች፦ | ||||||
Þ... |
የW መነሻ ከጎረቤቱ ከ «V» ነበር። ስለዚህ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ዋው» ከደረሱት 5 ፊደላት (F, U, V, W, Y) አንድ ነው።
በሮማይስጥ ፊደሉ «V» ወይንም /ኡ/ ወይንም /ው/ ሊወከል ይችል ነበር። ከ600 ዓም በኋላ በጀርመናዊ ቋንቋዎች ውስጥ ድምጹን /ው/ ለመጻፍ፣ ይደረብ ነበር እንደዚህ፦ VV። በየጥቂቱ ከ1550 በፊት ይህ የራሱ ፊደል «W» ተቆጠረ። ሆኖም በጣልኛ አይገኝም፣ በእስፓንኛ ወይም በፈረንሳይኛም አልፎ አልፎ በባዕድ ቃላት ይታያል፤ «W» የሚጠቀመው ግን በእንግሊዝኛ (ለ /ው/) እና ጀርመንኛ (ለ /ቭ/) ነው።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.