V
V / v በላቲን አልፋቤት 22ኛው ፊደል ነው።
የላቲን አልፋቤት | ||||||
---|---|---|---|---|---|---|
A | B | C | D | E | F | |
G | H | I | J | K | L | M |
N | O | P | Q | R | S | T |
U | V | W | X | Y | Z | |
ተጨማሪ ምልክቶች፦ | ||||||
Þ... |
የV መነሻ ከጎረቤቱ ከ «U» ነበር። ስለዚህ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ዋው» ከደረሱት 5 ፊደላት (F, U, V, W, Y) አንድ ነው።
በሮማይስጥ V አንድላይ ተነባቢውን «ው» ወይም አናባቢውን «ኡ» አመለከተ።
እንዲሁም ከዘመናት በኋላ ተነባቢውን «ቭ» ድግሞ ለማመልከት ቻለ። ቅርጹም ከ«U» ጋር ይለዋወጥ ነበር። ከ1378 ዓም በታየ በአንድ አልፋቤት ለመጀመርያው ጊዜ «U» (/ኡ/) እና «V» (/ቭ/) እንደ ልዩ ልዩ ፊደላት ተቆጠሩ። በ1754 ዓም የፈረንሳይ አካደሚ በይፋ «U» እና «V» እንደ ልዩ ልዩ ፊደላት ይቆጥራቸው ጀመር።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.