J

J / jላቲን አልፋቤት ፲ኛው ፊደል ነው።

የላቲን አልፋቤት
ABCDEF
GHIJKLM
NOPQRST
UVWXYZ
ተጨማሪ ምልክቶች፦
Þ...

ከ1516 አስቀድሞ፣ የላቲን ፊደል I ለተነባቢው «ይ»፣ ለአናባቢው «ኢ»፣ እና ለሮማይስጡ ቁጥር ፩ ተጠቀመ። ሆኖም በቃል መጨረሻ ሲደረብ እንደ -ii ሲጻፍ፣ ቅርጹ እንደ -ij ይምሰል ጀመር። ከ1516 ዓ.ም. ጀምሮ ቅርጹ «J» ለተናባቢው «ይ» እና ቅርጹ «I» ለአናባቢው «ኢ» ይለያዩ ጀመር።

የ«J» አጠራር በአውሮፓ ልሳናት፦ ሰማያዊ - «»፤ ቢጫ - «»፣ አረንጓዴ - «»፤ ቀይ - «»

ፈረንሳይኛ ግን የ«ይ» ድምጽ አጠራር ከዚያ በፊት እንደ «ጅ» ለመምሰል ስለ ጀመረ፣ እሱ ደግሞ በጥንታዊ ፈረንሳይኛና እንዲሁም በእንግሊዝኛ በ«I» ይጻፍ ነበር፣ ከ1625 ዓም ጀምሮ ግን በ«J» ይጻፍ ጀመር። እስካሁንም ድረስ «J» በእንግሊዝኛ እንደ «ጅ» ያሰማል፤ በፈረንሳይኛ ድምጹ እንደገና ተለውጦ አሁን እንደ «ዥ» ያሰማል። በዘመናዊ እስፓንኛ ግን J እንደ «ሕ» ያሰማል።

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.