3 መንቱሆተፕ

3 መንቱሆተፕ ሳንኽካሬ ግብጽን ከጤቤስ (11ኛው ሥርወ መንግሥት) የገዛ ፈርዖን ነበረ።

የ፫ መንቱሆተፕ ምስል

ሥነ ቅርስ ጉድለት ብዙ ስለ ፫ መንቱሆተፕ ድርጊቶች አይታወቅም። አንዳንድ ሕንፃ ከማሠራታቸው በላይ በተለይ የሚታወቀው በ2003 ዓክልበ. ግድም ወደ ፑንት አገር ለንግድ የላከው ተልእኮ ስለ ተከሠተ ነው። በአንድ ጽሑፍ ዘንድ ዓለቃው ሄኔኑና ፫ ሺህ ተጓዦች በየብስ እስከ ኮፕቶስ ከዚያም በመርከብ እስከ ፑንት ድረስ ሔዱ። ይህ ምናልባት የዛሬው ሶማሊላንድ ዙሪያ ይሆናል። ዕጣንሙጫ እና ሽቶ ይዘው ወደ ግብጽ ተመለሡ።

በ2002 ዓክልበ. ግድም በሞተበት ዓመት ልጁ 4 መንቱሆተፕ (ነብታዊሬ) ፈርዖን እንደ ሆነ ይታስባል።

ቀዳሚው
3 አንተፍ
ግብፅ ፈርዖን
2009-2002 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
4 መንቱሆተፕ
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.