2 ኤናናቱም
2 ኤናናቱም ከ2161 እስከ 2153 ዓክልበ. ግድም የላጋሽ ከተማ ንጉሥ በሱመር ነበር። አባቱን ኤንመተና ተከተለው። በእርሱ ዘመን የላጋሽ ተጽእኖ ይደክም ጀመር፣ ተከታዩም ኤነታርዚ ከቄሳውንት ወገን ሆኖ ለአዳብ ንጉሥ ሉጋል-አኔ-ሙንዱ መንግሥት ተገዥ እንደ ነበር ይመስላል።
ለ2 ኤናናቱም ብዙ ቅርሶች አይታወቁም። አንድ በር ማጠፊያ ላይ ያለው ቅርጽ ጽሁፍ 2 ኤናናቱም የመጥመቂያ ቦታ እንደ ከፈተ ያስታወቀናል።
ቀዳሚው ኤንመተና |
የላጋሽ ገዥ 2161-2153 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ ኤነታርዚ |
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.