2 ኤሪሹም
2 ኤሪሹም የአሹር ንጉሥ ነበር። ምናልባት 1730-1720 ዓክልበ. አካባቢ ገዛ። የናራም-ሲን (አሦር) ልጅና ተከታይ ይባላል።
የዓመት ስሞች
የያንዳንዱ አሦራዊ ዓመት ስም ለዚያ ዓመት የተሾመው የሊሙ ስም ነበረ። ከዚህ በታች የዓመቱ ሊሙ እና የሊሙ አባት ስም እንደ ኡልትራ አጭር አቆጣጠር ይዘርዝራሉ።[1]
«የማሪ ሊሙ ስሞች ዜና መዋዕል» (MEC) የተባለው ሰነድ ለዚህ ዘመን የሊሙ ስምና ተጨማሪ የዓመት ድርጊቶች ይሰጣል።[2] ይህም በታች ይመለከታል።
- 1730 ዓክልበ. - አሹር-ኤናም
- 1729 ዓክልበ. - እብኒ-እሽታር፣ ሲን-እሽመ-አኒ ልጅ - «ኢፒቅ-አዳድ ዓረፈ።»
- 1728 ዓክልበ. - አሹር-በል-ማልኪ፣ ኢዲን-አቡም ልጅ
- 1727 ዓክልበ. - በላኑም - «ኪርባና (?) <...>።»
- 1726 ዓክልበ. - ሱካሉም - «ሻምሺ-አዳድ <...> ።»
- 1725 ዓክልበ. - አሙር-አሹር - «ሻምሺ-አዳድ <...> ።»
- 1724 ዓክልበ. - አሹር-ኒሹ - «ሻምሺ-አዳድ <...> ።»
- 1723 ዓክልበ. - ማናዊሩም («እብኒ-አዳድ») - «ሻምሺ-አዳድ (ከካርዱኒያሽ ተመለሠ) ።»
- 1722 ዓክልበ. - ኢድናያ፣ አሹር-ኢሚቲ ልጅ
- 1721 ዓክልበ. - ዳዳያ / ፑዙር-ኒራሕ
- 1720 ዓክልበ. - አቢያ («አታማር-እሽታር») - «ሻምሺ-አዳድ (አሦርን ያዘ)።»
የአሦር ነገሥታት ዝርዝር (AKL) ደግሞ በናራም-ሲን ዘመን የተርቃ ንጉሥ 1 ሻምሺ-አዳድ ወደ «ካርዱኒያሽ» (ባቢሎን) (በስደት?) ሄዶ፤ በኋላም በ1723 ዓክልበ. ከባቢሎን ወጥቶ ኤካላቱምን እንደ ያዘ፣ በ1720 ዓክልበ. አሹርንም ይዞ ኤሪሹምንም አስወጥቶ ሻምሺ-አዳድ የአሦር ንጉሥ እንደ ሆነ ይዘግባል። በMEC እና በAKL ግን የሊሙ ስሞች ለነዚህ ዓመታት («እብኒ-አዳድ» እና «አታማር-እሽታር») ከታወቁት ሊሙ ስሞች ይለያያሉ፤ ምናልባት የኤካላቱም ሊሙዎች ነበሩ።
ቀዳሚው ናራም-ሲን |
የአሹር ገዥ 1730-1720 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ 1 ሻምሺ-አዳድ |
- የመስጴጦምያ ነገሥታት (ፈረንሳይኛ)
- የሊሙ ስሞች ዜና መዋዕል
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.