2
የቀይ የደም ሴሎች አማካይ እድሜ 120 ቀናት ሲሆን፥ አንድ ሰው ከ20 እስከ 30 ትሪሊየን ቀይ የደም ሴሎች ይኖሩታል። በተለያየ ምክንያት የጎደሉትን ለመተካት፥ በየሰከንዱ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ቀይ የደም ሴሎች መመረት ይኖርባቸዋል። ሰውነትን ለማዳረስ 20 ሰከንድ ብቻ ይፈጅባቸዋል፤ በሰውነት ውስጥ 25 ሚሊየን ሴሎች በሰከንድ ውስጥ ይመረታሉ። ሰውነታችን በየቀኑ 2 መቶ ቢሊየን ቀይ የደም ሴሎችን ያመርታል፤ የሆነ ነገር ሲነኩ ደግሞ በሰዓት 199 ኪሎ ሜትር በሆነ ፍጥነት ለአዕምሮ መልዕክት ይደርሰዋል። ደም በሰውነት ውስጥ በሚያደርገው ዝውውር በቀን 60 ሺህ ማይል ወይም 96 ሺህ 560 ኪሎ ሜትር ያክል ይጓዛል። የአንድ ሰው ልብ በህይዎት ዘመን 1 ሚሊየን በርሜል ደም ይረጫል። ሰውነት ውስጥ 5 ነጥብ 6 ሊትር ደም ሲኖር ይህ ደም በደቂቃ ሶሰት ጊዜ በሰውነት ውስጥ ይዟዟራል። ነርቭ በሰዓት 4 መቶ ኪሎ ሜትር በሆነ ፍጥነት መልዕክቱን ያደርሳል፤ ሲያስነጥሱ በሰዓት 166 ኪሎ ሜትር ፍጥነት ያለው ነፋስ ያመነጫሉ። በሚስሉ ጊዜ ደግሞ ፍጥነቱ ወደ 1 መቶ ኪሎ ሜትር ይወርዳል፤ ልብ በየቀኑ 1 መቶ ሺህ ጊዜ ይመታል። አይን እስከ 10 ሚሊየን ያክል የተለያዩ ነገሮችን መለየት የሚችል ሲሆን፥ ትልቅ ከተባለው ቴሌስኮፕ የተሻለ መረጃን የመያዝ አቅም አለው። ሳምባችን በቀን ከ2 ሚሊየን ሊትር በላይ አየር ወደ ውስጥ ይስባል፤ አጠቃላይ መጠኑ አንድ የሜዳ ቴኒስ መጫወቻ ሜዳን እንደሚያክልስ ያውቃሉ? አንድ ሰው ሲስቅ በትንሹ 36 ጡንቻዎችን ያሰራቸዋል፤ ከሰውነት አጠቃላይ ክፍል 70 በመቶው በውሃ የተሸፈነ ነው። አይንን ከፍቶ ማስነጠስ ከባዱ ነገር ነው። ሰውነት ላይ ካሉ ባክቴሪያዎች ብዙሃኑ በአፍ ውስጥ ይገኛሉ፤ በመቶ ሚሊየን የሚቆጠሩ ባክቴሪያዎች መሽገውበታል። በአንድ ስኩዌር ኢንች የሰውነት ክፍል ላይ 32 ሚሊየን ባክቴሪያዎች ይገኛሉ። ትልቁ የሰውነት ጡንቻ መቀመጫ ላይ ያለው ሲሆን፥ የጆሮ ጡንቻ ደግሞ ትንሹ ጡንቻ ነው። የአንድ ሰው ጭንቅላት በአማካይ 4 ነጥብ 5 ኪሎ ግራም ሲመዝን፤ አዕምሮው ደግሞ 1 ነጥብ 3 ኪሎ ግራም ይመዝናል። የአይናችን ኳስ 3 ነጥብ 5 በመቶ ያክሉ ክፍል ጨው ነው። 60 ሺህ 566 ሊትር ውሃ ደግሞ አንድ ሰው በህይዎት ዘመኑ ይጠጣዋል ተብሎ የሚታሰበው የውሃ መጠን ነው። ከሰውነት ፀጉር ውስጥ ቶሎ የሚያድገው ጺም ሲሆን፥ ከጉርምስና እስከሚያልፍበት ድረሰ ባይቆረጠው የአንድ ወንድ ጺም 9 ነጥብ 1 ሜትር ይረዝማል። እህል የሚያኝኩበት ጥርስዎ ከአለት እንደሚጠነክርስ ሰምተው ይሆን? ቀን ላይ ቴሌቪዥን እየተከታተሉ ከሚያጠፉት ይልቅ በመኝታ ሰዓት በርካታ መጠን ያለው ካሎሪ ያስወግዳሉ። ከሰውነት ውስጥ ማደግ የማያቆሙት አፍንጫና ጆሮ ናቸው፤ ሴት ልጅ ከወንድ በሁለት እጥፍ በበለጠ አይኗ ይርገበገባል። የሰው ልጅ በደቂቃ ውስጥ 6 ነጥብ 6 ሊትር አየር ይተነፍሳል። ከፍጥረታት ሁሉ ፊቱ ላይ በርካታ ጡንቻዎችን የታደለው የሰው ልጅ ሲሆን፥ በእያንዳንዱ የፊት ክፍል ላይ 22 ጡንቻዎች ይገኛሉ።