1 አሕሞስ

አሕሞስ (ግብጽኛ፦ /ያሕመስ/) በጥንታዊ ግብጽግብጽ አዲስ መንግሥትና የ18ኛው ሥርወ መንግሥት መሥራች ሲሆን ምናልባት 1558-1534 ዓክልበ. አካባቢ የገዛ ፈርዖን ነበረ። በዘመኑ ሂክሶስን ከግብጽ አባረራቸው።

አሕሞስ ነብፐሕቲሬ
አሕሞስ
አሕሞስ
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1558-1534 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ ካሞስ
ተከታይ 1 አመንሆተፕ
ባለቤት አሕሞስ-ነፈርታሪአሕሞስ-ሲትካሞስአሕሞስ ኸኑታመሁ
ሥርወ-መንግሥት 18ኛው ሥርወ መንግሥት
አባት ሰቀነንሬ ታዖ

የአሕሞስ ወንድም ካሞስ ካረፈ በኋላ አሕሞስ የደቡብ ግብጽ ብቸኛ ፈርዖን ሆነ። የዙፋን ስሙ ነብፐሕቲሬ ሆነ። በ1548 ዓክልበ. ገደማ በመጨረሻ አቫሪስን ከሂክሶስ ንጉሥ ኻሙዲ ያዘ። ሂክሶስ ከግብጽ ሸሽተው የዕብራውያን ነገደ ስምዖን ርስት የሆነውን ሻሩሄንን ያዙ። አሕሞስም በሻሩሄን ለ6 አመት ከብቦአቸው በ1542 ዓክልበ. ሻሩሄንን ያዘባቸው። ሻሩሄንን ከያዘ በኋላ ወደ ደቡብ ተመልሶ ቡሄንን በኖቢያኩሽ መንግሥት ያዘ። የጦር አለቃው የአሕሞስ ወልደ አባና ጽሑፍ እነዚህን ዘመቻዎች ይዘርዝራል።

ሌላ አለቃው አሕሞስ ፐን-ነኽበት በጽሑፉ ውስጥ ንጉሥ አሕሞስ በጃሂ (ፊንቄ) እንደ ዘመተ ይላል። በንጉሡ አሕሞስ 22ኛው አመት የተቀረጸ ጽሑፍ እንደሚል ከፊንቄ የተማረኩት በሬዎች የግንባታ ድንጋይ ለመሸከም ይጠቅሙ ነበር፤ ስለዚህ በፊንቄ የዘመተ ከ1536 ዓክልበ. ትንሽ በፊት እንደ ሆነ ይመስላል። ከፊንቄ የብርጭቆ ኢንዱስትሪ በግብጽ የተመሠረተው በዚህ ወቅት ያህል እንደ ሆነ ይታስባል።

አሕሞስ እንደ አባቱ በመምሰል ሦስቱን እኅቶቹን አገባቸው። መቃብሮቻቸውና የአሕሞስ ፒራሚድ ሁሉ ለሥነ ቅርስ ታውቀዋል። ልጁም 1 አመንሆተፕ በፈርዖንነት ተከተለው።

ፈርዖን ከመሆኑ በፊት የሚያሳይ የልዑል አሕሞስ ሐውልት


ቀዳሚው
ካሞስ
ግብፅ ፈርዖን
1558-1534 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
1 አመንሆተፕ
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.