1981
ክፍለ ዘመናት፦ | 19ኛ ምዕተ ዓመት - 20ኛ ምዕተ ዓመት - 21ኛ ምዕተ ዓመት |
አሥርታት፦ | 1950ዎቹ 1960ዎቹ 1970ዎቹ - 1980ዎቹ - 1990ዎቹ 2000ዎቹ 2010ሮቹ |
ዓመታት፦ | 1978 1979 1980 - 1981 - 1982 1983 1984 |
- ጥቅምት ፲፩ ቀን - የቀድሞው የፊሊፒንስ ፕሬዚደንት ፈርዲናንድ ማርቆስና ሚስታቸው ኢሜልዳ ማርቆስ በማጭበርበር ወንጀል ኒው ዮርክ ተከሰሱ።
- ኅዳር ፬ ቀን - በደብረ ታቦር፣ ጎጃም የተወለደው ሙሉጌታ ሥራው የሚባል የሃያ ስምንት ዓመት፣ በፖርትላንድ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተማሪ፣ በአሜሪካ ፖርትላንድ ከተማ በሦስት ፋሺስታዊ ሰዎች በዘረኝነት መነሻ ተቀጥቅጦ ሞተ። ነፍሱን ይማረው!!
- ኅዳር ፮ ቀን - የፍልስጥኤም ብሔራዊ ሸንጎ ሉዐላዊ ነጻ የፍልስጥኤም ግዛት አወጀ።
- ኅዳር ፯ ቀን - የኤስቶኒያ ምክር ቤት አገሪቱን ሉዐላዊ ሪፑብሊክ አድርጎ ደነገገ።
- ኅዳር ፳፫ ቀን - በፓኪስታን የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤናዚር ቡቶ የቃለ መሀላ ስነሥርዐት አከናውና ሥልጣን ተረከበች።
- ታኅሣሥ ፩ ቀን - በቀድሞው የሶቪዬት ሕብረት ግዛት ውስጥ በአርሜኒያ ክልል ውስጥ በተከሰተው የምድር እንቅጥቅጥ አርባ አምሥት ሺህ ሰዎች ሲሞቱ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ መኖሪያ ቤታቸውን አጥተዋል። ስፒታክ የምትባል የሃያ አምሥት ሺህ ነዋሪዎች ከተማ በዚሁ እንቅጥቅጥ ፈጽማ ወድማለች።
- ጥር ፲፭ ቀን - በቀድሞው የሶቪዬት ሕብረት ክልል ፤ በአሁኑ ታጂኪስታን ውስጥ የተከሰተ የመሬት እንቅጥቅጥ ፪፸፬ ሰዎች ገደል።
- ግንቦት ፭ ቀን - በቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግ፣ የቲያናማን አደባባይ ላይ በተማሪዎች የተመራ የረሀብ አድማ ተጀመረ።
- ነሐሴ 19 ቀን - ቮየጀር የተባለ ሰው ሰራሽ መንኮራኩር በኔፕቱን ፈለክ አለፈ።
- የማይክሮኔዥያ ተባባሪ ክፍላገሮች ዋና ከተማ ወደ ፓሊኪር ከኮሎኒያ ተዛወረ።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.