1924
ክፍለ ዘመናት፦ | 19ኛ ምዕተ ዓመት - 20ኛ ምዕተ ዓመት - 21ኛ ምዕተ ዓመት |
አሥርታት፦ | 1890ዎቹ 1900ዎቹ 1910ሮቹ - 1920ዎቹ - 1930ዎቹ 1940ዎቹ 1950ዎቹ |
ዓመታት፦ | 1921 1922 1923 - 1924 - 1925 1926 1927 |
- ጥቅምት ፯ - በአሜሪካ ውስጥ፣ በተለይም ሺካጎ ከተማ የሚኖረው ወንበዴ አል ካፖን «የቀረጥ ወንጀል» በመፈጸም ተከሶ የ፲፩ ዓመት እሥራት ተፈረደበት።
- ጥቅምት ፳፫ - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የአገሪቱን የመጀመሪያ ሕገ መንግሥት እንዲዘጋጅ አዝዘው በዘውዱ አንደኛ ዓመት በዓል በአዲሱ ምክር ቤት (ፓርላማ) ለሕዝብ ቀረበ።
- ታኅሣሥ - መኮንን እንዳልካቸው የአዲስ አበባ ከንቲባ ሆነው ተሾሙ።
- ታኅሣሥ ፲፭ - የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሕንፃ የመሠረት ድንጋይ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሲያስቀምጡ የእስክንድርያ ኮፕት ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ዮሐንስ እና የሀገር ጳጳሳትም በተገኙበት ልዩ ጸሎት እና ቡራኬ ተሠጥቶ ተመረቀ።
- መጋቢት 23 - አዶልፍ ሂትለር በቢር ሆል ፑች አመጽ በመሳተፉ የ5 ዓመት እስራት ተፈረደበት።
- የካቲት ፳፯ - አቡነ ባስልዮስ የአዲስ አበባ መንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም መምህርነት ተሰጣቸው።
- ጃፓን ማንቹርያን ወረረ፤ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሄርበርት ሁቨር በግፍና በወረራ የሚገኝ የመሬት ለውጥ ሁሉ አናከብርም የሚል ፖሊሲ አወጡ።
- ብላታ አየለ ገብሬ የውጭ ዜጎች ልዩ ፍርድ-ቤት ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ።
- የተስፋ ቁልፍ በጃማይካ በሌናርድ ሃወል «መጀመርያው ራስተፈሪ» ተጻፈ።
ልደት
- መስከረም ፳፯ - የደቡብ አፍሪቃው ጳጳስ እና የኖቤል የሰላም ሽልማት ተቀባይ ዴዝሞንድ ቱቱ በዚህ ዕለት ተወለዱ።
- ኅዳር ፮ - የኬንያው ፕሬዚደንት ምዋይ ኪባኪ
- የካቲት ፳፭ - የደቡብ አፍሪቃ ተወላጇ ዘፋኝ ሚሪያም ማኬባ በዛሬው ዕለት ተወለደች።
ዕለተ ሞት
- ጥቅምት ፰ - የኤሌክትሪክ መብራትን እንዲሁም አምፑልን በመፍጠር የሚታወቀው አሜሪካዊው ቶማስ አልቫ ኤዲሰን በ ኒው ጀርሲ ክልል ዌስት ኦሬንጅ ላይ በተወለደ በ ፹፬ ዓመቱ አረፈ።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.