13ኛው ሥርወ መንግሥት

13ኛው ሥርወ መንግሥትጥንታዊ ግብጽ የግብጽ ሁለተኛ ማዕከለኛ ዘመን ከ1819 እስከ 1646 ዓክልበ. ድረስ የቆየ ሥርወ መንግሥት ነው።

13ኛው ሥርወ መንግሥት በቀጥታ ከመካከለኛው መንግስት (12ኛው ሥርወ መንግሥት) ተቀጠለ፤ መጀመራው ፈርዖኑም የ4 አመነምሃት ልጅ እንደ ሆነ ይታመናል።[1] የግብጽ ታሪክ አዋቂ ኪም ራይሆልት እንደ ጻፈው፣ አዲስ ሥርወ መንግሥት መቆጠሩ (በማኔቶን አቆጣጠር) በስሜኑ ግብጽ ወይም ገሤም 14ኛው ሥርወ መንግሥት ተነስቶ ሀገሩ ስለ ተከፋፈለ ይመስላል፤ ይህም የሆነው በንግሥት ሶበክነፈሩ ዘመን ውስጥ እንደ ጀመረ ብሎ ያስባል።[1] ስለዚህ ከሜምፎስ በስሜን እስከ 2ኛው ፏፏቴ ድረስ ገዝቶ ነበር። በጊዜ ላይ የሥርወ መንግሥቱ ኃይል ደከመ፤ ሂክሶስም (15ኛው ሥርወ መንግሥት) ከወረሩ በኋላ ከጤቤስ ብቻ ይገዙ ጀመር። በ1646 ዓክልበ. ሂክሶስ መምፎስን ያዙ፤ አቢዶስም ከጤቤስ ነጻ ወጥቶ የራሱን የአቢዶስ ሥርወ መንግሥት መሠረተ፤ ስለዚህ ግዛቱ እንደገና ተከፋፍሎ መሪዎቹ ከዚያ በሚከተለው 16ኛው ሥርወ መንግሥት ይቆጠራሉ።[1]

ፈርዖኖች

ይህ ቅደም-ተከተል በተለይ እንደ አቶ ራይሆልት አስተሳሰብ ነው።

በሚከተለው ዘመን 8 ፈርዖኖች ቢገዙም፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም ጨቲ የሆነው ሰው አንኹ ዕውነተኛው ባለሥልጣን ይመስላል።

ከዚህ በኋላ ያሉት ከጤቤስ ውጭ አልገዙም።[2] ጸሃፊዋ ዳፍና በን ቶር እንደምታምን፣ ይህ የሆነው ሂክሶስ ያንጊዜ ከከነዓን ስለ ወረሩ ነው። ከመርነፈሬ አይ ቀጥሎ የግብጽ ሥራዊት ኃይል እጅግ ደክሞ ነበር ማለት ነው።[3]

ዋቢ መጻሕፍት

  1. Kim S. B. Ryholt, The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c.1800-1550 B.C., Museum Tusculanum Press 1997
  2. Thomas Schneider, "The Chronology of the Middle Kingdom and the Hyksos Period", in: E. Hornung/R. Krauss/D. Warburton (eds.), Ancient Egyptian Chronology (Handbook of Oriental Studies 1, 83), Leiden/ Boston 2006, p.180
  3. Daphna Ben Tor: Sequences and chronology of Second Intermediate Period royal-name scarabs, based on excavatedአ series from Egypt and the Levant, in: The Second Intermediate Period (Thirteenth-Seventeenth Dynasties), Current Research, Future Prospects edited by Marcel Maree, Orientalia Lovaniensia Analecta, 192, 2010, p. 91
  • Clayton, Peter A. Chronicle of the Pharaohs: The Reign-by-Reign Record of the Rulers and Dynasties of Ancient Egypt. London: Thames & Hudson Ltd., 2006.
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.