2002
፳፻፪ ዓመተ ምሕረት በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዘመነ ማርቆስ ሲሆን ዓመቱ ባለ ፫፻፷፭ ቀናት ዓመት ነው። ከመስከረም እስከ ነሐሴ ያሉት አሥራ ሁለቱ ወራት እያንዳንዳቸው ሠላሳ (፴) ቀናት ሲኖሩዋቸው አሥራ ሦሥተኛው የጳጉሜ ወር ደግሞ ፭ ቀናት አሉት።
ክፍለ ዘመናት፦ | 20ኛ ምዕተ ዓመት - 21ኛ ምዕተ ዓመት - 22ኛ ምዕተ ዓመት |
አሥርታት፦ | 1970ዎቹ 1980ዎቹ 1990ዎቹ - 2000ዎቹ - 2010ሮቹ 2020ዎቹ 2030ዎቹ |
ዓመታት፦ | 1999 2000 2001 - 2002 - 2003 2004 2005 |
የ ፳፻፪ ዓ/ም ዓቢይ ማስታወሻዎች
- መስከረም ፲፱ ቀን - በሳሞዋ ደሴቶች አጥቢያ የተከሰተው፣ በ ‘ሪክተር ሚዛን’ ስምንት ነጥብ ያስመዘገበው የመሬት እንቅጥቅጥ ‘ሱናሚ’ (tsunami) የሚባለውን የባሕር ነውጥ አስከተለ።
- ታኅሣሥ ፳፮ ቀን - በአሁኑ ጊዜ በ፰መቶ ፳፱ ነጥብ ፰ ሜትር ርዝመቱ በዓለም አንደኛው ሰማይ-ጠቀስ ሕንፃ የሆነው ቡርጅ ከሊፋ (Burj Khalifa (Arabic: برج خليفة)) ሕንፃ በዱባይ በዚህ ዕለት ተመረቀ።
- ጥር ፬ ቀን - በሀይቲ ደሴት ላይ ትልቅ የመሬት እንቅጥቅጥ ተነስቶ ፪ መቶ ፴ ሺህ ያህል ሰዎችን አጠፋ።
- ጥር ፯ ቀን - የፀሐይ ግርዶሽ በአዲስ አበባ ሰማይ ጧት ላይ ታየ።
- ጥር ፲፩ ቀን - በምስራቅ ጎጃም ዞን በሊበን ወረዳ ልዩ ስሙ ድጓም የደረብ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ አንዲት በግ የሚዳቋና የበግ ግልገሎች ተገላገለች።
- ጥር ፲፯ ቀን - ከቤይሩት ከተማ ፹፪ መንገደኞችንና ፰ አብራሪዎችና አስተናጋጆችን ጭኖ ወደአዲስ አበባ እያመራ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ፬፻፱ ቦይንግ ፯፻፴፯ አየር ዠበብ፣ ባልታወቀ ምክንያት ሜዲተራኒያን ባሕር ላይ ወድቆ ሲሰምጥ ፺ዎቹም ተሳፋሪዎች በሙሉ ተፈጅተዋል። ከነዚህ መኀል ፴፩ ኢትዮጵያውያን ነበሩ።
- መጋቢት ፭ ቀን - ዝነኛው የቀድሞ የክብር ዘበኛ ኦርኬስትራ ግጥምና ዜማ ደራሲ/አቀናባሪ ኮሎኔል ሣህሌ ደጋጎ አረፉ።
- መጋቢት ፲፩ ቀን - የአፍሪቃ ኅብረት የሠላምና ጸጥታ ምክር ቤት በማዳጋስካር ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል በለወጡ ግለሰቦችና ተቋማት ላይ የተጣለው ማዕቀብ ተግባራዊ እንዲሆን ወሰነ፡፡
- ሚያዝያ ፯ ቀን ለስድስት ቀናት፤ እንደገና ደግሞ በግንቦት ወር ኧያፍያትላዮኪውትል የተባለው የአይስላንድ እሳተ ገሞራ ፈንድቶ ብዙ አመድና ጢስ በአውሮጳ ከባቢ አየር ውስጥ አስገብቶ የአይሮፕላን በረራ በሰፊ አቋርጧል።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.