ፍቅር
ፍቅር ከልብ (ልቦና) ውስጥ የሚወጣ ጠንካራ የመውደድ ስሜት ነው። ፍቅር በብዙ አስተሳስቦች በኩል ልዩ ልዩ ትርጉሞች አሉት። ለምሳሌ «የሕይወት መዓዛ» ተብሏል።
ፍቅር በብሉይ ኪዳን
«ፍቅር እንደ ሞት የበረታች ናት» - መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 8፡6
በአይሁድም በክርስትናም በአንዳንድም ሌሎች ሃይማኖቶች በሚከብረው በብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ ፍቅረ ቢጽ በኦሪት ዘሌዋውያን 19፡18 ይታዘዛል፦ «ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ»... እንደገና ዘዳግም 10፡19፦ «እናንተ በግብፅ አገር ስደተኞች ነበራችሁና ስለዚህ ስደተኛውን ውደዱ።»
ሬጌ ፍቅር ነው ሁሌ። ረጋሳ ተጫኔ ሶሪ
በመጽሐፈ ምሳሌ ደግሞ፦ «የጎመን ወጥ በፍቅር መብላት የሰባ ፍሪዳን ጥል ባለበት ዘንድ ከመብላት ይሻላል።» - (15፡17) እናም ፍቅር ወሳኝ ነው
ፍቅር በአዲስ ኪዳን
የፍቅር ትርጓሜ በክርስትና የሚገኘው በቆሮንቶስ ፩፣ ምዕራፍ ፲፫ ነው። ፍቅር «ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም» በማለት ያሳስበናል (፲፫፡፮)።
ክርስቲያኖች የሚቀበሉት አዲስ ኪዳን ስለ ፍቅር በርካታ ተጨማሪ ትምህርት ይጠቅሳል። ለምሳሌም፦
- «ወዳጆች ሆይ፣ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፣ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፣ እርስ በርሳችን እንዋደድ።» -- 1 ዮሐንስ መልእክት 4፡7
- «እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፡ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።» -- 1 ዮሐንስ መልእክት 4፡1
- «ማንም፦ እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?» -- 1 ዮሐንስ መልእክት 4፡20
- «እግዚአብሔርን ስንወድ ትእዛዛቱንም ስናደርግ፡ የእግዚአብሔርን ልጆች እንድንወድ በዚህ እናውቃለን።» -- 1 ዮሐንስ መልእክት 5፡2
ፍቅር በፍልስፍና
ፍቅር እንደሞት ነው። ሞትን የምትፈራ ከሆነ ማፍቀር አትችልም። [1] ሬጌ ሁሌም ፍቅር ነው።
ፍቅር /love / በእርግጥ ስለፍቅር ብዙ ሰምተናል አይተናል እንድሁም አንብበናል ነገር ግን በፍቅርም ዓለም የምኖር ሰው አለ ለማለት አያስደፍርም ምክንያቱም በናፈቅር እንኳ ዘላቂ የሆነ በምክንያታዊነት የምንጠላቤት ሁነታ በሰዎች ህይወት ወይም ኑሮ ላይ ይታያልና በአጠቃላይ ፍቅር ማለት ትዕግስት ነው ፍቅር ማለት እውነት ነው ፍቅር ማለት ባለእንጀራውን እንደራሱ መወደድ ማለት ነው ፍቅር ማለት መልካምነት ነው ....... ፍቅር ማለት ካለ ምንም መተማመኛ ራስን አሳልፎ መስጠት ነው ።
- "ጥበብ ቅፅ 2 ገፅ 202"