ፋሲል መዋኛ
የፋሲል መዋኛ በጎንደር ከተማ ከፋሲል ግቢ 2 ኪሎሜተር በስተ ሰሜን ምዕራብ ርቆ የሚገኝ፣ በአጼ ፋሲለደስ ዘመን ተሰረቶ የነበረው የመዋኛ ስፍራ ነው (በአንዳንዶች ዘንድ በቀዳማዊ ኢያሱ ዘመን እንደተሰራ ይጠቀሳል)። በመዋኛ ስፍራው መካከል ላይ ያለው ባለ ሁለት ፎቅ ቤት የአጼ ፋሲል መኖሪያ እንደነበር ይገመታል። በአሁኑ ዘመን፣ ለጥምቀት በዓል የሚያገለግል ሲሆን ውሃ በምድር ውስጥ በተቆፈረ ቦይ ከቀሃ ወንዝ ያገኛል። በድሮ ጊዜ በአየር በተነፋ አቅማዳ እየተንሳፈፉ ሰዎች ይዝናኑ እንደንበርና ሁልጊዜም በውሃ የተመላ እንደነበር ይነገራል። ከአጠገቡ፣ በስተምስራቅ፣ የአጼ ፋሲለደስ ፈረስ የነበረው የዞብል መቃብር ይገኛል።
1.መኖሪያ ቤት 2.ዋናው በር 3. ውሃ ከቀሃ ወንዝ የሚመጣበት መሬት የተቀበረ ቦይ 4.ፋሲል መዋኛ ድልድይ 5. የአጼ ፋሲለደስ መኖሪያ 6.ፋሲል መዋኛ ገንዳ 7. ወደገንዳው የሚያስገቡ ደረጃዎች 8.ውሃ ማፍሰሻ ቦይ 9. ሁለተኛ በር 10. የዞብል መቃብር |
- የዓፄ ፋሲል መኖሪያ 1920ዎቹ
ፋሲል መዋኛ | |
![]() | |
የአጼ ፋሲለደስ መኖሪያና መዋኛው በ ፋሲል መዋኛ | |
![]() ![]() ፋሲል መዋኛ | |
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.