ፋርስ
ፋርስ አገር (ፋርስኛ፦ ایران /ኢራን/) ወይም የኢራን ኢስላማዊ ሬፑብሊክ (جمهوری اسلامی ایرا /ጆምሁሪ-የ ኤስላሚ-የ ኢራን) በእስያ ውስጥ የሚገኝ አገር ነው። ዋና ከተማው ቴህራን ነው።
ፋርስ እስላማዊ ሪፐብሊክ |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: مهر خاوران | ||||||
ዋና ከተማ | ቴህራን | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ፋርስኛ | |||||
መንግሥት መሪ ፕሬዝዳንት ምክትል ፕሬዝዳንት |
እስላማዊ ሪፐብሊክ ዓሊ ኽሃመነኢ ሓስሳን ሮኡሃኒ ዐስሃቅ ጃሃንጊሪ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) |
1,648,195 (17ኛ) 0.7 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2016 እ.ኤ.አ. ግምት |
82,800,000 (18ኛ) |
|||||
ገንዘብ | ፋርስ ሪኣል ﷼ | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +3:30 | |||||
የስልክ መግቢያ | +98 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ | .ir ایران. |
ስም
ለኗሪዎቹ የሀገር ስም ከጥንት ጀምሮ ኢራን ሲሆን ከአገር ውጭ እንደ ፋርስ ወይም በመሰለ ስያሜ ይታወቅ ነበር።
በ1927 ዓም ሻህ (ንጉስ) ሬዛ ሻህ ሀገሩ በውጭ አገራት ዘንድ «ኢራን» በመባል እንዲታወቅ ጠየቀ። (በዚህም ወቅት ያህል ደግሞ በመንግሥታት ማኅበር መሃል የኢትዮጵያ ስያሜ በ1923 ዓም ከ«አቢሲኒያ» ተቀየረ፤ የታይላንድም በ1932 ዓም ከ«ሲያም» ተቀየረ።)
በ1951 ዓም ግን ልጁ ሻህ ሙሃመድ ሬዛ ፓሕላቪ ሁለቱ ስያሜዎች (ኢራን እና ፋርስ) አንድላይ በመለዋወጥ ትክክለኛ እንደ ተቆጠሩ አዋጀ።
ኢራን
ዞራስተር ባዘጋጀው በአቨስታ ዘንድ ሕዝቡ «አይርያ» (አርያኖች) ይባላሉ፤ መጀመርያ አገር ቤታቸው «አይርያነም ቫይጃህ» ሲባል ይህ በአራስ ወንዝ አካባቢ እንደ ተገኘ ይታመናል።[1] ከዚህ መጀመርያ አገር በኋላ የተከተሉት አገራት በአፍጋኒስታንና በፋርስ አካባቢ ሲገኙ ይህም አውራጃ በጥንት «አሪያና» እና «አሪያ» ይባል ነበር። ሄሮዶቶስ 480 ዓክልበ.ግ. የሜዶን ብሔር ድሮ ስም «አሪዮይ» እንደ ነበር መሰከረ፤ የፋርስ አሓይመኒድ ነገስታት እንደ ፩ ዳርዮስ ብሔራቸውን «አሪያ» አሉት። ከሳሳኒድ ሥርወ መንግሥት ጀምሮ (218 ዓም) በመካከለኛ ፋርስኛ የሀገሩ ኗሪ ስም «ኤራን» ወይም «ኢራን» ሆኗል።