ጨረቃ ላይ መውጣት

ጨረቃ ላይ መውጣት የምንለው ማናቸውም ሰው ሰራሽ መንኮራኩሮች ጨረቃ ገጽ ላይ ሲያርፉ ያለውን ክንውን ነው። ይህ እንግዲህ ሰውንም ሆነ ያለሰው የተደረጉ በጨረቃ የማረፍ ክንውኖችን ይጠቀላላል። ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰራሽ የሆነ ነገር ጨረቃ ላይ ያረፈው በመስከረም 13፣ 1959 እ.ኤ.አ. ሲሆን ይኸውም የሶቭዬት ህብረት ሉና 2 ሚሲዮን ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ የሰው ልጅ እራሱ ጨረቃ ላይ የወጣው ሐምሌ 20፣ 1969 እ.ኤ.አ. ሲሆን ይኸውን በአሜሪካው የአፖሎ 11 ሚሲዮን መንኮራኩር ነበር። ባጠቃላይ 24 አሜሪካውያን ወደጨረቃ ተጉዘዋል፣ 12ቱ የጨረቃን ምድር በእግራቸው ረግጠዋል።

በዚህ ወቅት ሶቪየት ህብረትም የራሷን ጠፈርተኞች ለመላክ ሞክራለች። ለዚህ እንዲረዳት ጨረቃ ላይ አራፊ LK የተሰኘ መንኮራኩር ሰራች፣ ሆኖም ግን ይህን መንኮራኩር ወደ ጨረቃ የሚወስድ ከባድ ሃይል ያለው ሮኬት ከአሜሪካ ቀድማ መስራት ስላልቻለች ተቀደመች። ይህም በነበራት የጨረቃ ላይ ማረፍ ፍላጎት ቀዝቃዛ ውሃ ቸለሰበት። ከዚህ በታቸ ለጨረቃ ጉዞ ሶቪየቶች አዘጋጅተውት የነበረ ልኬ የተሰኘው መንኮራኩር ይታያል።

አሜሪካን ሚሽን የመንኮራኩሩ ገፊ ጠፈርተኞች የተነሳበት የሚሽኑ አላማ የሚሽኑ ውጤት
አፖሎ 10 ሳተርን ፭ ቶማስ ስታፎርድ, ጆን ያንግ, ዩጂን ኬማን 18 ግንቦት 1969 በጨረቃ ዙሪያ መሽከርከር ተሳካ ከጨረቃ መሬት በ15.6 km ርቀት ጨርቃን ዞሩ፣ ይህም በሰው ልጆች ለመጀመሪያ ለሁለተኛ ጊዜ ጨረቃ መዞሩ ነው
አፖሎ 11 ሳተርን ፭ ኔል አርምስትሮንግ, ማይክል ኮልንስ, በዝ አልድሪን 20 ሐምሌ 1969 ጨረቃ ላይ ማረፍ! ተሳካ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰው ልጅ የጨረቃን ምድር ረገጠ። ኔል አርምስትሮንግ ለመጀመሪያ የጨረቃን ምድር የረገጠው ሰው ሆነ።
አፖሎ 12 ሳተርን ፭ ፒት ኮንራድ, ሪቻርድ ጎርደን, አለን ቢን 14 ህዳር 1969 ጨረቃ ላይ ማረፍ ተሳካ መንኮራኩሪ ከመነሳቱ በፊት በመብረቅ ተመታ ሆኖም ጉዳቱ እምብዛም ስላልነበር ወደ ጨረቃ ተጓዘ።ጨረቃ ላይ አረፈ። ጠፈርተኞቹም በጨረቃ ላይ ተረማመዱ
አፖሎ 13 ሳተርን ፭ ጂም ላቨል, ጃክ ስዋይጋርት, ፍሬድ ሄሴ 11 ሚያዚያ 1970 ጨረቃ ላይ ማረፍ ውድቀት [1] መንኮራኩሩ ገና መሬት ላይ እያለ መዋዠቅ ጀመረ። ቀጥሎም ትናንሽ ፍንዳታወች እና የእሳት አደጋ ስለደረሰበት ጨረቃን አንዼ ዙሮ ሲያበቃ ምድሯ ላይ ሳያርፍ ወደመሬት ተመለሰ። ጠፈርተኞቹ ግን አልተጎዱም
አፖሎ 14 ሳተርን ፭ አለን ሸፓርድ, ስቱዋርት ሩሳ, ኤድጋርድ ሚሼል 31 ጥር 1971 ጨረቃ ላይ ማረፍ ተሳካ የመጀመሪያው የቀለም ምስል ተነሳ። በሶፍትዌር ስህተት ምክንያት ሚሽኑ ለተወሰነ ጊዜ ቢተጓጎልም መንኮራኩሩ ግን ጨረቃ ላይ አርፎ ጠፈርተኞች የተለያዩ ፈተናወችን በጨረቃ ምድር ላይ አካሂደዋል
አፖሎ 15 ሳተርን ፭ ዴቪድ ስኮት, አልፍሬድ ዋልደን, ጄምስ ኤርዊን 26 ሐምሌ 1971 ጨረቃ ላይ ማረፍ ተሳካ - ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረቃ ላይ ለ3 ቀን ተቆየ፣ የመጀመሪያውን የጨረቃ ላይ መኪና በመጠቀም 27.7 ኪሎሜተር ጉዞ ተደረገ
አፖሎ 16 ሳተርን ፭ ጅኦኝ ይኣኝጝ, ኬን ማቲንግሊ, ቻርለስ ዱክ 16 ሚያዚያ 1972 ጨረቃ ላይ ማረፍ ተሳካ የጨረቃን ደጋማ ክፍል አጠኑ። ከ3 ቀን በላይ መቆየት አልተቻለም በመንኮራኩሩ ችግር ምክንያት
አፖሎ 17 ሳተርን ፭ ዩጂን ከርናን, ሮናልድ ኤቫንስ, ሃሪሰን ሽሚት 7 ታህሳስ 1972 ጨረቃ ላይ ማረፍ ተሳካ የመጨረሻው የሰው ልጅ ጨረቃን የረገጠቅ በዚህ ሚሽን ነው። ከዚህ በኋላ ተቋረጠ። ዩጂን ከርናን የጨረቃን ምድር የረገጠው የመጨረሻው ሰው ነው።

ዋቢ ጽሁፎች

  1. "Apollo 13 - A Successful Failure". Archived from the original on 2018-01-03. በ2010-10-27 የተወሰደ.
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.