ጥቅምት ፳፮
ጥቅምት ፳፮ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፶፮ኛ ቀን ነው። ከዚህ ቀን በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፫፻፲ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፱ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - በኢትዮጵያ እና በታላቋ ብሪታኒያ መኻል የስልክ ግንኙነት ተጀመረ። አገልግሎቱ በወቅቱ ከሰኞ እስከ ዓርብ ብቻ ከጧቱ ፭ ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊቱ ፮ ሰዓት ከሩብ ድረስ የተወሰነ ሲሆን ከብሪታኒያ በደቂቃ አንድ ፓውንድ ስተርሊንግ ከሩብ (£1.25) ይፈጅ ነበር።
- ፲፱፻፺፫ ዓ.ም. - በደርግ ዘመን ሕይወታቸው የጠፋው የመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የቀብር ስርዐታቸው ተፈጸመ።
- ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. - የቀድሞው የኢራቅ ፕሬዚደንት ሳዳም ሁሴን በአገራቸው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተመሠረተባቸው ክስ በሰው ዘር ላይ አድርገዋል በተባሉባቸው ወንጀሎች ኃላፊነታቸው ተረጋግጦ የስቅላት ሞት ተፈረደባቸው።
- ፳፻ ዓ.ም. - የቻይና ሕዝባዊ ሬፑብሊክ የመጀመሪያዋ የጠረፍ መንኲራኩር በጨረቃ ዙሪያ መንሳፈፏን ጀመረች።
ልደት
ዕለተ ሞት
ዋቢ ምንጮች
- (እንግሊዝኛ) The London Gazette;[p 6281], 28th day of October, 1954
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.