ጥቅምት ፳፩

ጥቅምት ፳፩ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፶፩ኛው እና የመፀው ፳፮ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፲፭ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፲፬ ቀናት ይቀራሉ።


ታሪካዊ ማስታወሻዎች

  • ፲፰፻፶፯ ዓ.ም. -በአሜሪካ ደቡብ ምዕራብ የምትገኘው የነቫዳ ክልል የሕብረቱ ሠላሳ ስድስተኛ አባል ሆነች።
  • ፲፱፻፸፯ ዓ.ም. - የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኢንዲራ ጋንዲ በሁለት የሲክ የጥበቃ ወታደሮቻቸው እጅ ተገደሉ። ይሄንንም ሁኔታ ተከትሎ በኒው ዴሊ በፈነዳው የሕዝብ ሽብር ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ የሲክ ተወላጆች ሕይወታቸውን አጡ።

ልደት

  • ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. - ቦናንዛ በሚባለው የአሜሪካ የቴሌቪዥን ትርዒት ላይ ሊትል ጆን ካርትራይትን ሆኖ በመጫወት በዓለም ስመጥሩነትን ያተረፈው ተዋናይ ማይክል ላንደን

ዕለተ ሞት

  • ፲፱፻፺፱ ዓ.ም. - በደቡብ አፍሪቃአፓርታይድ ዘመን ፕሬዚደንት የነበሩት ፒ. ደብልዩ ቦታ በተወለዱ በዘጠና ዓመታቸው አረፉ።

ዋቢ ምንጮች


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.