ጥቅምት ፲፰

ጥቅምት ፲፰ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፵፯ኛው ቀን ነው። ከዚህ ቀን በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፫፻፲፰ ቀናት በዮሐንስ፤ በማቴዎስ፤ እና በማርቆስ ዘመናት ደግሞ ፫፻፲፯ ቀናት ይቀራሉ

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

  • ፵፯ ዓ/ም - በጥንታዊት የሮማ ንጉዛት፣ ኔሮ የቄሳርነት ዘውድ ጭኖ ነገሠ።
  • ፲፭፻፳፬ ዓ.ም. - የአምባሰል ጦርነት፦ በአህመድ ኢብን ኢብራሂም አል-ጋዚ ግራኝ አህመድ የሚመራው የአዳል ሠራዊትና በኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ልብነ ድንግል ሠራዊት መኻል በተደረገው ጦርነት የግራኝ አህመድ ወገን አሸነፈ። የደቡብ ኢትዮጵያ ግዛቶችም በአዳሎች ቁጥጥር ስር ዋሉ።
  • ፲፱፻፵፰ ዓ/ም - ለመንግሥት እንግዶች ማስተናገጃ፤ ለአገር ጎብኝዎች ማረፊያና ፤ለሕዝብ መጠቀሚያ ሆኖ እንዲያገለግልና ገቢውም ለቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል መርጃ እንዲሆን በማሰብ፣ ቀድሞ «ፍል ውሃ ፓላስ» አሁን የግዮን ሆቴል ተብሎ የሚጠራው ሆቴል በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመርቆ ተከፈተ። [1]

ልደት

፲፱፻፸፬ ዓ.ም ሐረር ቢራበመብራት ኃይል፤ በኢትዮጵያ ቡና የ እግር ኳስ ቡድኖች እንዲሁም በየመን አል ሻአብ ቡድን በተከላካይነት መደብ የሚሰለፈው ኳስ ተጫዋች ሰሎሞን መልካሙ አንዳርጋቸው

ዋቢ መጻሕፍትና ሌላ ምንጮች

  1. አበራ ጀምበሬ፤ «የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የበጎ አድራጎት ድርጅት መመሥረት»፣ አዲስ አበባ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት (፲፱፻፶፪ ዓ/ም)፤ ገጽ ፹፩-፹፪


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.