ጥቅምት ፲፯

ጥቅምት ፲፯ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፵፯ኛው ቀን ነው። ከዚህ ቀን በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፫፻፲፱ ቀናት በዮሐንስ፤ በማቴዎስ፤ እና በማርቆስ ዘመናት ደግሞ ፫፻፲፰ ቀናት ይቀራሉ

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

፲፱፻፱ ዓ.ም. የወሎው ንጉሥ፤ የልጅ እያሱ አባት ንጉሥ ሚካኤል የልጃቸውን ከሥልጣን መውረድ አዋጅ ተቃውመው በጦር ኃይል ለማክሸፍ ከነሠራዊታቸው ወደ አዲስ አበባ ሲዘምቱ በአልጋ ወራሹ ራስ ተፈሪ መኮንን መሪነት እና በጦር ሚኒስቴሩ በፊታውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስ አበጋዝነት የዘመተው ሠራዊት በሰገሌ ጠራ ሜዳ ወረዳ ላይ ገጥመው ከ፭ ሰዐት ውጊያ በኋላ የወሎ ሠራዊት ድል ሆነ። ንጉሡም ተማረኩ። [1]

፲፱፻፶፩ ዓ.ም. በፓኪስታን የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ኢስካንደር ሚርዛ በ ጄኔራል አዩብ ካን በሚመራ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ወረዱ።

፲፱፻፷፬ ዓ.ም. የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ስሟን ቀይራ ዛይር ተብላ ተሰየመች።

፲፱፻፸፩ ዓ.ም ሦስተኛው የግብጽ ፕሬዚደንት አንዋር ሳዳት እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ሜናኽም ቤጊን የዓመቱ የኖቤል የሠላም ሽልማት ተሸላሚዎች መሆናቸው ይፋ ሆነ።

ልደት

፲፱፻፵፰ ዓ.ም የማይክሮሶፍት መሥራችና ባለጸጋው የአሜሪካ ዜጋ ቢል ጌትስ

ዕለተ ሞት

ዋቢ መጻሕፍትና ሌላ ምንጮች

  1. ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ "ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ ፩ኛ መጽሐፍ


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.