ግዕዝ ኣልቦ

ግዕዝ ኣልቦ ፊደል በላቲኑ ወይም ኣረቡ ኣልቦ ኣኃዝ ("0") ምትክ እንዲያግለግል የተሠራ ኣዲስ የኣኃዝ ምልክት ነው። የግዕዝ ፊደል ከጥንት ፊደላት ኣንዱ ስለሆነ የኣልቦ ቍጥር ምልክት ከሌላቸው ፊደላት ኣንዱ ነበር። ፊደሉን ለሟሟላት ግዕዝን ኮምፕዩተራይዝ ሲያደርጉ ዶ/ር ኣበራ ሞላ የግዕዝን ኣልቦ ፈጥረው ከ፴ ዓመታት በላይ ጥቅም ላይ ውለዋል።

ኣልቦው ጥቅም ላይ እንዲውል ዶክተሩ ከ"1" እስከ "9" ተጨማሪም ኣኃዞች በመጨመር የግዕዝን ቍጥሮች ብዛት ከ፳ ወደ ፴ ከፍ ኣድርገዋቸዋል። የዶክተሩ ኣሥር ኣዳዲስ የግዕዝ ቍጥራዊ (Numeric) ኣኃዞች ከኣንድ እስከ ዘጠኝ ከኣሉት የዩኒኮድ መደብ ውስጥ የገቡት ዘጠኙ ጥንታዊ ፊደላዊ (Alpahbetic) ኣኃዞች እንዲለዩ በቅርቡ መቀመጫዎቻቸውን ኣንስተዋል። ይህ ከግዕዝ ቀለሞች ጠባይም ጋር የሚሄድ ነው። ምክንያቱም ቍጥራዊና ፊደላዊ ኣኃዞች ቅርጾች መጋራት ስለሌለባቸውም ነው። ዶክተሩ ከዩኒኮድ በፊት የፈጠሩት የኣልቦ ቍጥራዊ ኣኃዝ መቀመጫ የኣለው ቀለም ሲሆን ከዩኒኮድ በኋላ በቅርቡ የጨመሯቸው ከኣልቦ እስከ ዘጠኝ የኣሉት መቀመጫ የሌላቸው ኣዳዲስ ኣሥር ቍጥራዊ ኣኃዛት ናቸው። ስለዚህ የዶክተሩ ኣልቦ ኣኃዞች ሁለት ዓይነቶች ናቸው። ዶክተሩ የግዕዝ ኣልቦ ኣኃዝ ቀለሞችና የግዕዝ ኣሥር ቤት ኣኃዛዊ ቍጥሮች ፈጣሪም ናቸው። እነዚህ ግኝቶችና ኣጠቃቀሞቻቸው በፓተንት ማመልከቻቸውም ተጠቅሰዋል።

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.