ግንቦት ፳
ግንቦት ፳ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፷ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፶፭ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፮ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፭ ቀናት ይቀራሉ።
ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፰፻፹፯ ዓ/ም - የአየርላንድ ተወላጁ ደራሲና ባለቅኔው ኦስካር ዋይልድ (Oscar Wilde) በግብረ ሰዶማዊነት ተፈርዶበት ታሰረ።
- ፲፱፻፵፮ ዓ/ም - ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በዚህ ዕለት ለአሜሪካን 'ሴናተሮች' እና የሕዝብ ተወካዮች ጥምር ሸንጎ ንግግር አደረጉ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የጠቅላይ ሚኒስትር እንዳልካቸው መኮንን መንግሥት የሚኒስትሮችን ለውጥ ይፋ አደረገ። ከነዚህም አንዱ የአገር ግዛት ሚኒስትር የነበሩትን ደጃዝማች ዘውዴ ገብረ ሥላሴን ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መዛወር ያካትታል።
ልደት
ዕለተ ሞት
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.