ግንቦት ፫
ግንቦት ፫ ቀን፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፵፫ኛው ዕለት ሲሆን፤ የፀደይ (በልግ)ወቅት ፴፰ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፻፳፫ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፻፳፪ ቀናት ይቀራሉ።
ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፱፻፲፮ ዓ/ም - ሁለቱ ጀርመናውያን ተሽከርካሪ አምራቾች፣ ጎትሊብ ዴይምለር እና ካርል ቤንዝ ኩባንያዎቻቸውን አዋሕደው አዲሱን የመርሴዲስ-ቤንዝ (Mercedes-Benz) ኩባንያ መሠረቱ።
- ፲፱፻፵፰ ዓ/ም- የብሪታኒያ የቅኝ ግዛቶች ሚኒስትር የምዕራብ አፍሪቃዋ ጎልድ ኮስት (በኋላ ጋና) ነጻነቷን እንደምትሰጥ መወሰኑን ለሕዝብ ተወካዮች ሸንጎ አስታወቀ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ “የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጣልቃ ገቦች በአገሪቱ ጉዳይ ውስጥ እየገቡ አስቸግረዋል በሚል መነሻ የፈረንሳይን፤ አሜሪካን፤ ግብጽን፤ የሶቪዬት ሕብረትን፤ የብሪታኒያን እና የዩጎዝላቪያን የልዑካን አለቆች ሰብስበው አነጋገሩ። በማግሥቱ ይፋ የተደረገው ጽሑፋዊ ቃለ-ጉባኤ አምባሳደሮቹ የተጠሩት “የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት በአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ጉዳዮች ላይ የባዕዳንን ጣልቃ ገብነት በብርቱ እንደሚቃወም እና በኢትዮጵያ ግዛትና ሉዐላዊነት ላይ የሚሰነዘሩትን ማናቸውንም እርምጃዎች ለመከላከል ቆራጥ መሆኑን እንዲገነዘቡ ነው።” ይላል።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከግብጽ ፕሬዚደንት ሳዳት ጋር ለውይይት ወደካይሮ ሲጓዙ፣ እግረ መንገዳቸውን ካርቱም ላይ አርፈው ከፕሬዚደንት ኒሜሪ ጋር ተለወያዩ።
ልደት
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.