ጋፋት

ጋፋትደቡብ ጎንደርደብረ ታቦር ትንሽ ወጣ ብላ የምትገኝ ቦታ ናት። በዚች ቦታ ከጥንት ጀምሮ አንጥረኞችና የእጅ ጥበብ አዋቂወች ይኖሩበት እንደነበር ትውፊት አለ። ሆኖም ግን በታሪክ ትልቅ ቦታን ያገኘቸው በ19ኛው ክፍለ ዘመን ዓፄ ቴዎድሮስሴባስቶፖል መድፍን የአውሮጳ ሚስዮናውያን የአካባቢውን አንጥረኞችንና ቀጥቃጮችን በማሰለፍ በዚህ ቦታ አስርተው በማስመረቃቸው ነው። ከሴባስቶፕል በተጨማሪ 8 ሌሎች መድፎች ተሰርተው እንደነበር እና ላያቸው በአማርኛ በተጻፉ ጥቅሶች ያጌጡ እንደነበር ሚሲዮኑ ቴዎፍሎስ ዋልድማየር መዝግቧል። [1]

ጋፋት በአጼ ቴወድሮስ ዘመን - ከመቃጠሉ በፊት

ይህ ቦታ የዚያን ዘመኑን የስራ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ቅሪቶች ብዙ የሉትም። ምክንያቱም ንጉሱ ወደ መቅደላ ሲሄዱ ከተማውን አቃጥለውት ነበርና።

  1. Erlebnisse in Abessinien in den Jahren 1858-1868 ገጽ 82-86
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.