ጉዛራ

የጉዛራ ቤተመንግስትእምፍራዝ በስተደቡብ 5ኪሎሜትር ወጣ ብሎ የተሰራ ግምብ ነው። ይሄውም በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ፣ ከጣና ሐይቅ በስተ ስሜን ምስራቅ መሆኑ ነው።

ጉዛራ
የጉዛራ ቤተ መንግስት
ጉዛራ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ጉዛራ

12°10′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°43′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

አጼ ሚናስ የክረምት ጊዜን በጉባኤ፣ ጉዛራ አካባቢ ማሳለፍን ልማዳቸው ማድረጋቸው በታሪክ ይጠቀሳል። የጉዛራ ግምብ 18ሜትር በ12 ሜትር ሲሆን፣ በድሮ ዘመን ግምቡን የሚከልል ሰፊ አጥር ነበር። የግምቡ ስራ በ1562ዓ.ም. የተጠናቀቀ ሲሆን አጼ ሠርፀ ድንግል በምጽዋ ቱርኮች ላይ ድል መቀዳጀታቸውን አስመልክቶ ለመታሰቢያነት ያስገነቡት ነበር። [1][2] በ1563ዓ.ም. አጼ ሠርፀ ድንግልበጌምድርንና የትግሬን አስተዳዳሪዎች በዚሁ ቦታ አነጋግረው እንደነበር በታሪክ ይጠቀሳል።

የጉባኤ ከተማ ከ1570 ጀምሮ እስከ 1581 ድረስ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ በመሆን ቢያገለግልም በመጨረሻ ግን ንጉሱ ጉዛራን ለቀው ወደሰሜን በማቅናት አይባዋና ከተማቸው አደረጉ። የሆኖ ሆኖ የጉዛራ ቤተመንግስት ከጎንደር ከተማ ቀደምት ምሳሌ የሆነ ነበር።

የጉዛራ ቤተመንግስት በ1880ዓ.ም.
የጉዛራ ቤተመንግስት አቅድ

ማጣቀሻ

  1. Monti della Corte, I Castelli di Gondar, 1938, pp. 105-108
  2. http://iscte.pt/~mjsr/html/expo_jesuits/architecture/guzara_and_dabsan_.htm


This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.