ጉሬዛ

ተራ ጉሬዛ (ሮማይስጥColobus guereza) ኢትዮጵያአፍሪካ ውስጥ የሚገኝ ዝንጀሮ ነው።

?ጉሬዛ

ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ
ስፍን: ጉንደ እንስሳ (Animalia)
ክፍለስፍን: አምደስጌ (Chordata)
መደብ: አጥቢ (Mammalia)
ክፍለመደብ: ሰብአስተኔ
አስተኔ: የምሥራቅ ክፍለአለም ዝንጀሮች
ወገን: የጉሬዛ ወገን Colobus
ዝርያ: ጉሬዛ
ክሌስም ስያሜ
''Colobus guereza''
ኤዷርድ ሪውፐል፣ 1835 እ.ኤ.አ.
የጉሬዛ መኖሪያ ስፋት
የጉሬዛ መኖሪያ ስፋት
ጉሬዛ

የእንስሳው ሳይንሳዊ ጸባይ

ጉሬዛ ወገን ውስጥ የተዛመዱት ዝርዮች ጥቁር ጉሬዛ (ኢኳቶሪያል ጊኔ ዙሪያ)፣ የአንጎላ ጉሬዛ (አንጎላኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክታንዛኒያ)፣ ንጉሥ ጉሬዛ (ሴኔጋል ዙሪያ)፣ ነጭ-ጭን ጉሬዛ (ጋና ዙሪያ) ናቸው። የተዛመዱት ወገኖችም ቀይ ጉሬዛዎችወይራ ጉሬዛ ከኢትዮጵያ ውጭ ይገኛሉ። እነዚህ ዝንጀሮች ሁሉ ደግሞ «ኮሎበስ» ተብለው ከሌሎች ዝንጀሮች የሚለዩበት አውራ ጣት በመጎደላቸው ነው። የሚበሉት በተለይ ያልበሰለ ቡቃያ ሲሆን፣ እነዚህ ዝንጀሮች ብቻ የሚያመሰኳ ሆድ አላቸው።

አስተዳደግ

ጉሬዛ በተለይ ቅጠልን እንዲሁም ፍራፍሬን ይበላል፤ አንዳንዴም እንጨት፣ ያትክልት ዘር፣ አበባ፣ አፈርም ወይም ጋጥመ-ብዙ ይበላል።

ጉሬዛ የምግብ ሰንሰለት አካል እንዲሆን የተፈጠረ አውሬ ይመስላል። በተለይ በንሥር እንዲሁም በግስላ ይነጠቃል፤ ከኢትዮጵያም ውጭ ሐለስት ቺምፓንዚ ያድነዋል። ሐለስት ግን ከሁሉ ቀይ ጉሬዛን ይመርጣል።

የእንስሳው ጥቅም

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.