ገንዘብ
በአንድ አገር ወይም ማህበረሰብ ውስጥ ለሸቀጥ (አሰፈላጊ እቃ) ና አገልግሎት መግዢያ እንዲሁም እዳ መክፈያ የሚያገለግ ማንኛውም ነገር ሁሉ ገንዘብ ይባላል።
የጥንቱ ገንዘብ ዋጋ ይመነጭ የነበረው ከራሱ ከተሰራበት እቃ ዋጋ ነበር (ለምሳሌ፡ ከወርቅ የተሰራ ሳንቲም) ። በዚህ ምክንያት እንዲህ አይነቱ ገንዘብ የኮሞዲቲ ገንዘብ ይባላል። በአሁኑ በአለማችን የሚሰራባቸው ገንዘቦች በራሳቸው የራሳቸው የሆነ ዋጋ የላቸውም (ለምሳሌ ከተልባ እግር የተሰራው ዶላር በራሱ ዋጋ የለውም) ። ይህ አይነት ገንዘብ ፊያት ገንዘብ ሲባል ዋጋው የሚመነጨው የአንድ አገር መንግስት ህጋዊ መገበባያ ብሎ ስላወጀው ብቻ ነው። ህጋዊ መገበባያ ሲባል ለማንኛውም በዚያ አገር ውስጥ ላለ እዳ ይህ የታወጀው ገንዘብ እንደ ክፍያ ሲቀርብ "አይ! አልቀበልም" ማለት ክልክል ነው። በዚህ ምክንይት የፊያት ገንዘብ ዋጋ ከመንግስት ሃይል ጋር ከፍተኛ ግንኙነት አለው።
ያንድ ዘመናዊ ሃገር የገንዘብ አቅርቦት በሁለት ይከፈላል፣ ይኸውም ተጨባጭ የሆነው የታተመው ብርና በማይጨበጥ መልኩ በባንክ ቤት ተጠራቅሞ ያለው በቼኪንግ እና ሴቪንግ የሚከፈለው የባንክ ሒሳብ ነው። ባብዛኛው ጊዜ እኒህ የ ባንክ ሒሳቦች ታትሞ ከቀረበው ብር በላይ ናቸው። በምናባዊ አለም ውስጥ የተቀመጡት እነዚህ የቁጥር ሰነዶች ምንም እንኳ የማይታዩና የማይዳሰሱ ቢሆንም ልክ እንደ ጥሬ ብር እኩል ለመሸጥና ለመለወጥ ያገለግላሉ። [1][2] [3]
ታሪክ
- የጥንቶቹ ሰወች እቃን በቃ በመለዋወጥ መገበያየት ቻሉ። ይህም በማይተዋወቁ ሰወች ዘንድ ነበር። በሚተዋወቁ ግን የስጦታ ልውውጥ ይደረግ ነበር።[4]
- ቀስ ብሎ የተለያዩ ባህሎች ኮሞዲቲ ገንዘብ መጠቀም ጀመሩ። ከሁሉ አስቀድሞ ከብትና እህል (ገብስ) መደበኛ ነበሩ። በተለይ ዛጎል በብዙ ህብረተሶቦች ዘንድ እንደ መገበባያ ገንዘብ ይጠቅም ነበር። [5] መዳብ፣ ብረት፣ ብርና ወርቅ በክብደት ለመግዣ ቢጠቀሙም፣ ሰዎች ውዱን ብረታብረት ከርካሹ ጋራ ስላቀላቀሉት በአማካኝ ጥረቱ እየቀነሰ ሄደ።
- በ660 ዓክልበ. ያሕል ጥረቱን እንዲመረምሩ የፈተና ደንጊያ ዕውቀት ስላገኙ ለመጀመሪያ ጊዜ የወርቅ ሳንቲም እና የብር ሳንቲም መጠቀም የጀመሩት ልድያውያን ነበር።.[6] በኢትዮጵያም በአክሱም ነገሥታት የታተሙ የወርቅ ሳንቲሞች ስራ ላይ ውለዋል።
- ከዚህ ቀጥሎ የተነሳው ተወካይ ገንዘብ የሚባለው ገንዘብ አመጣጡ እንዲህ ነው። ወርቅና ብር ነጋዴወች ለደንበኞቻቸው ደረሰኝ በመጻፍ፣ ያንን ደረሰኝ ደምበኞች በማምጣት በፈለጉት ሰዓት ወርቁንና ብሩን ማግኘት ቻሉ። ቀስ በቀስ ደረሰኙ በወርቁና በብሩ ቦታ ተተክቶ እንደ ሙሉ ገንዘብ መስራት ጀመረ። የወረቀት ገንዘብ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው በሶንግ ስርወ መንግስት (970 ዓ.ም. - 1276 ዓ.ም.) ዘመን በቻይና አገር ነበር፣ ብሮቹም ያወዚ ይባሉ ነበር፣ አመጣጣቸውም ከላይ እንደተገለጸው የደረሰኝ ጽሁፈትን ተከትሎ ነው። አውሮጳ ውስጥ የወረቀት ገንዘብ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው በ1661፣ ስዊድን አገር ነበር። በዚህ ወቅት እያንዳንዱ ጥሬ የወረቀት ብር ወደ ተወሰነ የወርቅ ክብደት የሚቀየርበት ስሌት ነበረው።
- ሆኖም ስዊድን የወረቀት ብር ያወጣው ምክንያት ጦርነት ለማድረግ ፈልጎ በቂ ወርቅ ወይም ሌላ ገንዘብ በአገሩ ስላልነበረው ነው። አሁን ወዲያው የስዊድን መንግሥት ፈቃዱን እንዲፈጽሙ ሥራተኖች መክፈል ቻለ። በጥቂት ዓመት ውስት የስዎድን ወረቀት ገንዘብ ወደቀ። ነገር ግን ከትንሽ በኋላ የእንግላንድ መንግሥት በፈረንሣይ ላይ በጦርነት ተይዞ ለጦርነትም ያህል በቂ ሀብት ባለመኖሩ እንዲህ አይነት መፍትሄ መረጡ፤ የኢንግላንድ ፓውንድ ድፍን ጀመሩ። ስለዚህ ከዚህ በኋላ አገራት ፈቃዳቸውን ለመፈጽም አዲስ የወርቅ ወይም የብር ማዕድን ማግነት አስፈላጊ አልነበረም። በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ይህ በወርቅ የተደገፈ የተሰኘው የገንዘብ ስርዓት በይፋ በመላው ዓለም ተንሰራፋ።
- ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በብሬቶን ውድስ ስብሰባ፣ አብዛኞቹ የአለማችን አገሮች ፊያት ገንዘብን በማጽደቅ ገንዘባቸውን በቀጥታ በወርቅ ከመደገፍ ይልቅ ከአሜሪካን ዶላር አንጻር እንዲተረጎም አደረጉ። የአሜሪካን ዶላር በተራው በወርቅ የተደገፈ ነበር።
- በ1971 የአሜሪካን መንግስት ዶላሩን በወርቅ መደገፍ/መተርጎም አቆመ። ከዚህ በኋላ ሌሎቹም አገሮች የየራሳቸውን ገንዘብ ከአሜሪካን ዶላር አንጻር መተርጎም አቆሙ። በአሁኑ ወቅት አብዛኛው የአለማችን ገንዘቦች በወርቅም ሆነ በሌላ ቋሚ ነገር የሚደገፉ ሳይሆን በየአገሩ ባሉ መንግስታት እንደ ህጋዊ መገበባያ በወጡ አዋጆች ምክንያት ነው።
የገንዘብ አይነቶች
ማጣቀሻ
- "Learn More About Coins and Money Treasure Trove - Philadelphia Fed". Philadelphia Fed.. በ2009-04-20 የተወሰደ.
- "On2 Money / A History of Money". Pbs.org. Archived from the original on 2009-03-08. በ2009-04-20 የተወሰደ.
- Bernstein, Peter, A Primer on Money and Banking, and Gold, Wiley, 2008 edition, pp29-39
- Graeber, David. 'Toward an Anthropological Theory of Value'. pp. 153-154.
- Kramer, History Begins at Sumer, pp. 52–55.
- Herodotus. Histories, I, 94