ገምል

ገ ጉ ጊ ጋ ጌ ግ ጎ ጓ ጐ ጒ



አቡጊዳ ታሪክ

ገምልአቡጊዳ ተራ ሦስተኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓንአራማያና በዕብራይስጥ ፊደሎች ሦስተኛው ፊደል «ግመል» በሶርያም ፊደል «ገመል» ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል «ጂም» ተብሎ በ«አብጃድ» ተራ 3ኛ ነው። (በዘመናዊ ተራ ግን 5ኛው ነው።) በግሪክም 3ኛው ፊደል «ጋማ» ይባላል። በነዚህ ቋንቋዎች አጠራሩ «ግ» ሲሆን በዓረብኛ ግን «ጅ» ሆኗል።

የ«ግ» ድምጽ በቋንቋ ጥናት «ነዛሪ የትናጋ ፈንጂ» ይባላል።[1]

ታሪክ

ተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕል ቅድመ-ሴማዊ ሣባ ግዕዝ
T14


የገምል መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ «የሚጣል ምርኩዝ» ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር፤ አጠራሩ ግን «ቀመእ» ነበር። በግብፅ የሠሩት ሴማውያን ግን በቋንቋቸው «ገምል» ስላሉት፣ ይህ ስዕል «ግ» ሆኖ እንዲሰማ መጣ። «ግመል» ደግሞ የእንስሳ አይነት ሊሆን ይችላል።

ከነዓን አራማያ ዕብራይስጥ ሶርያ ዓረብኛ
ገምል ገምል ג ገምል


የከነዓን «ግመል» እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ «ግመል» የአረብኛም «ጂም» ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት «ጋማ» (Γ γ) አባት ሆነ፤ እሱም የላቲን አልፋቤት (C c) , (G g) እና የቂርሎስ አልፋቤት (Г, г) እና (Ґ, ґ) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ«ገምል» ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር (ሦስት) ከግሪኩ Γ በመወሰዱ እሱም የ«ገ» ዘመድ ነው።

  1. "የግዕዝ መረጃ ከኢኦተቤ ማህበረ ቅዱሳን". Archived from the original on 2014-10-13. በ2015-04-22 የተወሰደ.
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.