ዶ/ር ይስሓቅ ዳልኬ
ዶ/ር ይስሓቅ ዳልኬ በ1949 እ.ኤ.አ. በወላይታ ተወለዱ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በጄኔራል ዊንጌት ት/ቤት በከፍተኛ ውጤት በመጨርሳቸው ከጃንሆይ የወርቅ ሰዓት በመሸለም ተመርቀው በአዲስ አበባ ሕክምና ፋካሊቲ ትምህርታቸውን በመቀጠል የዶክተሬት ድግሪያቸውን እንዳገኙ ጥቂት ወራት በጎንደር እንዳገለገሉ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አሜሪካን አገር ሄደው ትምህርታቸውን በአጥጋቢ ሁኔታ ጨርሰው እካሁንም ኑሮአቸውንም በአሜሪካን አገር በፍሎሪዳ አርገዋል። ዶ/ር ይስሃቅ ባሁኑ ጊዜ በዩኒቨርስቲ ኦፍ ፍሎሪዳ አስተማሪና ረዳት ፕሮፌስር ሆነው ከማገልገላቸውም በላይ ኔልሰን ማንዴላና የቀድሞ ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን ባቋቋሙት ዓለም አቀፍ የኤች አይ ቪ ኤይድስ ፋውንዴሺን የአሜሪካንን ሕክምና ባለሙያዎችን ይወክላሉ። ዶ/ር ይስሓቅ ከፓናማ ተወላጅ ከሆኑት ባለቤታቸው የ2 ወንዶችና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ናቸው።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.