ዶሮ
ዶሮ መብረር የማትችል የአእዋፍ ዘር ናት። የሰው ልጅ ካለመዳቸው እንስሳት አንዷ ዶሮ ስትሆን የሰው ልጅ ሥጋዋንና ዕንቁላሏን በመብላት ይጠቀማል። ዶሮ ተወዳጅና በብዛት የሚገኝ
በአጠቃላይ ከ13 ቢልዮን የሚበልጡ ዶሮዎች እንዳሉ ይገመታል! እንዲሁም ሥጋው በጣም ተወዳጅ በመሆኑ በየዓመቱ ከ33 ቢልዮን ኪሎ ግራም በላይ ለምግብነት ይውላል። ከዚህም በተጨማሪ ዶሮዎች በዓለም ዙሪያ በአንድ ዓመት ውስጥ 600 ቢልዮን ገደማ እንቁላሎችን ይጥላሉ። ዶሮ በምዕራባውያን አገሮች በብዛት የሚገኝ ሲሆን ዋጋውም ርካሽ ነው።
የዶሮ ታሪክ
ዶሮ የእስያ ቀይ የዱር ጅግራ ዝርያ ነው። ሰው ዶሮን በቀላሉ ማልመድ እንደሚችል ለመረዳት ጊዜ አልፈጀበትም። ዶሮና እንቁላል ለገበያ ለማቅረብ ሲባል በሰፊው የዶሮ እርባታ የተጀመረው ከ19ኛው መቶ ዘመን በኋላ ነው። የዶሮ ሥጋ ዛሬ በብዙዎች ዘንድ በጣም ተወዳጅ ምግብ ነው። የከተማ ነዋሪዎችን ጨምሮ በሚልዮን የሚቆጠሩ ቤተሰቦች ለራሳቸውም ሆነ ለገበያ ለማቅረብ ዶሮ ያረባሉ። ብዙ አገሮች ለራሳቸው አገር የአየር ጠባይ የሚስማሙና ጥሩ ምርት የሚሰጡ የዶሮ ዝርያዎችን አራብተዋል። ከእነዚህ መካከል የአውስትራሊያው አውስትራሎፕ፣ መጀመሪያ በሜድትራኒያን የተገኘውና አሁን በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በብዛት ያለው ሌግሆርን፣ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚረቡት ኒው ሃምፕሻየር፣ ፕላይማውዝ ሮክ፣ ሮሜ አይላንድ ሬድ እንዲሁም ውያንዶቴ፤ የእንግሊዞቹ ኮርኒሽ፣ ኦርፒንግቶን እና ሱሴክስ የሚባሉት ጥቂቶቹ ናቸው። በእርባታ ረገድ የተገኘው የተሻሻለ ሳይንሳዊ ዘዴ ዶሮ እርባታ ስኬታማ የግብርና ኢንዱስትሪ እንዲሆን አስችሎታል። የዩናይትድ ስቴትስ ገበሬዎች የዶሮ በሽታን በሳይንሳዊ መንገድ ከመቆጣጠራቸው በተጨማሪ አመጋገባቸውንና አሰፋፈራቸውን በተመለከተ ጥንቃቄ በተሞላበት ዘዴ ክትትል ያደርጋሉ። አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ያለውን በገፍ የማርባት ዘዴ እንደ ጭካኔ ይቆጥሩታል። ይሁን እንጂ ይህ አመለካከት ገበሬዎቹ በየጊዜው ይበልጥ ውጤታማ የሆኑ የዶሮ ማራቢያ ዘዴዎችን ከመፈለግ አላገዳቸውም። ዘመናዊው ዘዴ አንድ ሰው ብቻውን ከ25, 000 እስከ 50, 000 የሚያክሉ ዶሮዎችን እንዲያረባ ያስችላል። አንድን ዶሮ ለገበያ ለማድረስ የሚወስደው ጊዜ ሦስት ወር ብቻ ነው። [1]
Notes
- ኬንያ የሚገኘው የንቁ! ዘጋቢ እንደጻፈው