ድንች

ድንች በስሩ የሚያፈራ እና ፍሬው ለምግብነት የሚውል የተክል አይነት ነው።[1] (ሮማይስጥSolanum tuberosum) መጀመርያ በቅድመ-ታሪክ የታረሰ በፔሩ አገር ደቡብ አሜሪካ ነበር። ከ1500 ዓም በፊት በአውሮፓ አልታወቀም። በዓለም ላይ ከሩዝ፣ ከስንዴና ከበቆሎ ቀጥሎ አራተኛ ተፈላጊ ምግብ ድንች ነው።[2]

ድንች

ወደ ኢትዮጵያ እንዴት ገባ?

ድንች ወደ ኢትዮጵያ እንደ አውሮፓዊያን የዘመን ቀመር በ1858 እ.ኤ.አ በጀርመን ተወላጅ የእጽዋት ባለሙያ (Botanist) ዶክተር ቪልሄልም ሺምፐር አማካኝነት እንደገባ መዛግብት ያስረዳሉ።[3] ድንች በመጀመሪያዎቹ 40 አመታት ልክ እንደ ሌሎች የአውሮፓና የአፍሪካ ሀግራት በኢትዮጵያውያን የምግብ ሥርአት ውስጥ ውስጥ በቀላሉ ተቀባይነትን ቶሎ አላገኘም ነበር። ይሁን እንጂ በዚሁ ክፍለ ዘመን ማብቂያ ማለትም በ1900 ዓ.ም ላይ አገሪቱን ክፉኛ በመታው ድርቅ ምክንያት ድንች እንደ አንድ የምግብ አማራጭ ሰዎች መጠቀም በመጀመራቸው ለድንች መስፋፋት መልካም አጋጣሚን ፈጥሮ አልፏል። ይህ በሂደት ጠቀሜታው የታወቀው ሰብል ከ152 አመታት በኋላ እ.ኤ.አ. በ2010 በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስሌጣን የተካሄደው ዓመታዊ የግብርና ምርት ቅኝት ዘገባ 164, 000 ሄክታር መሬትን በመሸፈን 940,209 ቶን ምርት የተሰበሰበበት ደረጃ ላይ ደርሷል[3]። ይህም በሀገሪቱ ውስጥ ምን ያህል ተቀባይነት ለማግኘት እንደቻለ ያስረዳል።

እንዴት ይመረታል?

ድንች ከባህር ወለል በላይ እስከ 4000 ሜትር ከፍታ ባላቸው ቦታዎች ላይ ለመብቀል ይችላል። ይሁን እንጂ ከ1800 - 3500 ሜትር ከፍታ ለተክሉ እድገትም ሆነ ምርታማነት ይበልጥ ይስማማዋል።[3] ድንቹ በደንብ በደረቀ አፈር ውስጥ ይበቅላል ነገር ግን ረግረጋማ አፈርን አይወዱም።[4]


  1. https://dictionary.abyssinica.com/%E1%8B%B5%E1%8A%95%E1%89%BD
  2. https://www.ethiopianreporter.com/52262/
  3. https://www.agrobig.org/documents/2.1_Potato_agronomy_and_post_harvest_handling_Manual.pdf
  4. https://am.potatoes.news/potato-farming-planting-care-harvesting-a-full-guide/Daily-News
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.