ዱሙዚድ፣ አሣ አጥማጁ

ዱሙዚድ «አሣ አጥማጁ»ሱመር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ የኡሩክ ሦስተኛ ንጉሥ ነበረ። ከሉጋልባንዳ ቀጥሎና ከጊልጋመሽ በፊት 100 አመታት እንደ ነገሠ ይላል። ከዚህ በላይ የኪሽ ንጉሥ ኤንመባራገሲ በዱሙዚድ እጅ እንደ ተማረከ ይነግራል።

በሱመር አፈ ታሪክ ስለ ኡሩክ ንጉሥ ዱሙዚድ ዘመን የሚያወሩ በርካታ ሰነዶች ተገኝተዋል። በነዚህ ጽላቶች ውስጥ ግን የቅጽል ስሙ «አሣ አጥማጁ» ሳይሆን፣ የኡሩክ ንጉሥ ስም «ዱሙዚድ እረኛው» ይባላል። ነገር ግን በነገሥታት ዝርዝር ላይ፣ ሁለት ልዩ ልዩ ነገሥታት «ዱሙዚድ» ተብለዋል፤ እነርሱም ከማየ አይኅ በፊት በባድ-ቲቢራ የነገሠው «እረኛው» እና ከማየ አይኅ በኋላ በኡሩክ የነገሠው «አሣ አጥማጁ» ናቸው። ታሪኩ በነገሥታት ዝርዝሩ ላይ ትንሽ እንደ ተደባለቀ ይመስላል።

ጽላቶቹ እንደሚሉት፣ ይህ የኡሩክ ንጉሥ ዱሙዚድ በቅንጦት እየተቀመጠ፣ ድሆችና ረኅብተኞች ሰዎች (ወይም «ከይሲዎች» እንደሚባሉ) በአመጽ ተነሡበት። እንዳይዟት፣ ቁባት ባለሥልጣኗ ኢናና በርሷ ፋንታ ዱሙዚድን በመክዳት ወደ እጃቸው ሠጠችውና ሤረኞቹ ከዚያ ገደሉት።[1] የሚከተለውም የኡሩክ ንጉሥ ጊልጋመሽ በነገሥታት ዝርዝር ላይ «አባቱ ከይሢ የሆነ» ይባላል።

በኋለኛ አረመኔ እምነት፣ ዱሙዚድ እንደ ጣኦቱ ተሙዝ፣ ቁባቱም ኢናና እንደ ሴት ጣኦት እሽታር ይታወሱ ነበር። ስለ ተሙዝም ሞት በየአመቱ በብዙ ልቅሶ ማስታወሻ በዓል ይደረግ ነበር።

  1. የዱሙዚድ ተረቶች፣ በእንግሊዝኛ ትርጉምና በኦሪጂናል ሱመርኛ
ቀዳሚው
ሉጋልባንዳ
ኡሩክ ንጉሥ (ሉጋል)
2400-2382
ዓክልበ. ግድም
(መቶ በአፈ ታሪክ)
ተከታይ
ጊልጋመሽ
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.