ዮፍታሄ ንጉሤ
ግራ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ (፲፰፻፺፯ ዓ.ም. በደብረ ኤልያስ ቀበሌ፣ ጎጃም ተወልደው ሰኔ ፴ ቀን በ፲፱፻፴፯ ዓ.ም. አረፉ[1]) ስመ ጥር ኢትዮጵያዊ ደራሲ ነበሩ። እኚህ ታላቅ ደራሲ በርካታ ድርሰቶችን የጻፉ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች አብዛኛዎቹ ለሕትመት አልበቁም።
የመጀመርያውን የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር “ኢትዮጵያ ሆይ ደስ ይበልሽ በአምላክሽ ኃይል በንጉሥሽ” የሚለውን የደረሱት ቀኝጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ፤ ስለአገር ፍቅርና ጀግንነት የሚያወሱ በርካታ ድራማዎችና መዝሙሮችን የደረሱ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል “አፋጀሽኝ”፣ “እለቄጥሩ” ወይም “ጎበዝ አየን” ይገኙበታል። ከድል በኋላ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ከ፲፱፻፴፭ ዓ/ም እስከ ሕልፈታቸው ድረስ አገልግለዋል። የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር እና የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በመታባበር ጳጉሜ ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ የተመረቁትን እና የቀኝ-ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤን እንዲሁም የደራስያን፤- ነጋድራስአፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ እና አቶ [[ተመስገን ገብሬን ምስል የተቀረጸባቸው ቴምብሮችን ገበያ ላይ አውለዋል።[2]
የድርሰት ሥራዎች
- ተአምራዊው ዋሽንት (፲፱፻፳፫ ዓ/ም)
- ጎበዝ አየን (፲፱፻፳፰ ዓ.ም.) * ምስክር (፲፱፻፴ ዓ/ም)
- ጥቅም ያለበት ጨዋታ (፲፱፻፴፩ ዓ/ም)
- ሙሽሪት ሙሽራ
- ያማረ ምላሽ
- የሆድ አምላኩ ቅጣት (፲፱፻፴፪ ዓ/ም)
- ዳዲ ቱራ (፲፱፻፴፫ ዓ/ም)
- የህዝብ ጸጸት (፲፱፻፴፬ ዓ/ም)
- ሙሾ በከንቱ (፲፱፻፴፭ ዓ/ም)
- አባት ንጉሳችን ጠረፍ ይጠብቅ (፲፱፻፴፭ ዓ/ም)
- የደንቆሮዎች ቲያትር (፲፱፻፴፮ ዓ/ም)
- አፋጀሽኝ (፲፱፻፴፮ ዓ/ም)
- ዓለም አታላይ (፲፱፻፵፩ ዓ/ም)
- እያዩ ማዘን (፲፱፻፵፪ ዓ/ም)
- ንጉሡ እና ዘውዱ (፲፱፻፵፮ ዓ/ም)
ማጣቀሻ
- መዝገበ ህትመት ዳሰሳ፣ ገጽ 13
- ‘ሪፖርተር’ Ethiopian Reporter, “የአራት ደራስያን መታሰቢያ ቴምብሮች ታተሙ” 09 SEPTEMBER 2012
ዋቢ ምንጮች
- (እንግሊዝኛ) «History of Ethiopian Theater» Archived ሴፕቴምበር 29, 2007 at the Wayback Machine በዮናስ ሃይለመስቀል. ፌብሩዋሪ 20 ቀን 2007 ታይቷል።
- «Bibliography of Ethiopian Writers» Archived ጁላይ 20, 2011 at the Wayback Machine ከብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻህፍት ኤጀንሲ - ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር (pdf)
- ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ መዝገበ ህትመት ዳሰሳ፣ ቅፅ 25፣ ቁጥር 5፣ 2000 ዓ.ም. Archived ጁላይ 20, 2011 at the Wayback Machine
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.