ዮካይድ ማክ ኤይርክ

ዮካይድ (ወይም ዮኩ) ማክ ኤይርክአየርላንድ ልማዳዊ አፈ ታሪክ ዘንድ ከፊር ቦልግ የአየርላንድ ከፍተኛ ንጉሥ ነበር። ዮካይድ የሪናል ማክ ጌናን ልጅ ኤይርክ ልጅ ነበር። ሚስቱ ታይልቲው ነበረች፤ እርሷም የእስፓንያ ንጉሥ «ማግ ሞር» ወይም «ማድሞር» ልጅ ትባላለች። ዋና ከተማው ከእርሷ ታይልቲን ተባለ።

ሴንጋን ማክ ዴላ ልጅ ፎድብገን አይርላንድን ለ፬ ዓመታት ገዝቶ በኤይርክ ማክ ሪናል ልጅ ዮካይድ ዕጅ ወድቆ ተገልብጦ ዮካይድ የዛኔ ከፍተኛ ንጉሥነቱን ያዘበት።

ሌቦር ገባላ ኤረን («የአይርላንድ ወረራዎች መጽሐፍ»፣ 1100 ዓ.ም. ግድም) እና በ1625 ዓ.ም. አካባቢ የታተመው የሴጥሩን ኬቲን ታሪክ መጽሐፍ የአይርላንድ ታሪክ እንዳለ፤ በዮካይድ ዘመን ከጠል በቀር ዝናብ አልነበረም፤ አንዳችም ዓመት ያለ መከር ግን አልነበረም። እንዲሁም «ሀሠቶች ከአየርላንድ በዘመኑ ተባረሩ፤ በእርሱ መጀመርያው ሕገ ፍትሕ ተፈጸመና» ይሉናል።

ዮካይድ ፲ አመት ከገዛ በኋላ የነመድ ሌሎች ተወላጆች የሆነው ወገን ቱዋጣ ዴ ዳናን ወርረው ፊር ቦልግን በማግ ትዊረድ ውግያ ድል አደረጓቸውና ዮካይድና መቶ ሺህ ፊር ቦልግ ተገደሉ። የቀሩት ፊር ቦልግ ወደ ስኮትላንድ ደሴቶች ሸሹ። የቱዋጣ ዴ ዳናን ንጉሥ ኑዋዳ እጅ ስለ ተቋረጠ፣ ለ፯ ዓመታት እስኪዳን ድረስ ብሬስ የአይርላንድ ከፍተኛ ንጉሥ ሆነ።


ቀዳሚው
ፎድብገን
አይርላንድ (ኤልጋ) ከፍተኛ ንጉሥ
1511-1501 ዓክልበ. (አፈታሪክ)
ተከታይ
ብሬስ
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.