ያንጎን
ያንጎን (ቡርምኛ፦ ရန္ကုန္မ္ရုိ့) አንድ ታላቅ ከተማ በምየንማር (የቀድሞው 'ቡርማ') ነው። የምየንማ ዋና ከተማ እስከ 1998 ዓ.ም. ነበረ። በመጋቢት 17 ቀን 1998፣ የምየንማ መንግሥት ኔፕዪዶ አዲሱ ዋና ከተማ መሆኑን አዋጀ።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 4,344,100 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 16°47′ ሰሜን ኬክሮስ እና 96°10′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
'ያንጎን' ማለት ከ'ያን' ('ጠላት' ወይም 'ጥላቻ') እና ከ'ኮውን' ('አልቋል') ተወሰደ። ስለዚህ የከተማው ስም 'ጥላቻ (ወይም ጠላቶች) አልቀዋል' ለማለት ነው። መጀመርያ በ6ኛ ክፍለ ዘመን በሞን ሕዝብ ሲመሠረት ስሙ ዳጎን ነበር። በ1745 ዓ.ም. ንጉሡ አላውንግፓያ አውራጃውን አሸንፎ ስሙን ወደ ያንጎን ቀየረው። እንግሊዞችም በ1844 ከተማውን በጦርነት ሲይዙ ስሙን ራንጉን አሉት። ይህ ስም በይፋ በ1981 ዓ.ም. ወደ ያንጎን ተመለሠ።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.