የፈርዖኖች ዝርዝር

የግብጽ ፈርዖኖች ዝርዝር በሥርወ መንግሥታት አከፋፈል እንደ ተለመደ ከማኔጦን የተወረሰ ነው። በተጨማሪ አንዳንድ ሌላ ጥንታዊ ዝርዝር ምንጭ ይታወቃል። ለመሆኑ ለብዙዎች ፈርዖኖች በሥነ ቅርስሃይሮግሊፍ መዝገብ በመገኘቱ፣ የስሞቻቸው አጠራር በግብጽኛ አሁን ሊታወቅ ይችላል። ለብዙዎቹም አያሌ ልዩ ስሞች አሏቸው።

ጥንታዊው መንግሥት

የጥንታዊ መንግሥት ዘመኖች ቁጥር በትክክል ሊታወቅ አይችልም። ከጥንታዊው ዘመን በኋላ የመካከለኛው መንግሥት (ምሥር) ፈርዖኖች መጀመርያ የገቡት 2130 ዓክልበ. ግድም ስለ ሆነ፣ ጥንታዊው መንግሥት ከዚያው በፊት መጨረስ ነበረበት። ነገር ግን ለያንዳንዱ ፈርዖን የዘመነ መንግሥታቸው ዕድሜዎች በየምንጩ እጅግ ይለያልና በጠቅላላ ምን ያህል ጊዜ እንደ ፈጀ ለማለት ያስቸግራል። በአንዳንድ ሊቃውንት ግምት ዘንድ የተመሠረተው 3200-3100 ዓክልበ. ግድም ቢሆንም፣ ይህ ግመት ብቻ መቅረቱ ማስታወስ ያሻል።

ከ1ኛው ሥርወ መንግሥት አስቀድሞ በደቡብ የነገሡት አለቆች

1ኛው ሥርወ መንግሥት

2ኛው ሥርወ መንግሥት

3ኛው ሥርወ መንግሥት

4ኛው ሥርወ መንግሥት

5ኛው ሥርወ መንግሥት

6ኛው ሥርወ መንግሥት

7ኛው ሥርወ መንግሥት

ማኔጦንና ሌሎቹ ጥንታዊ ምንጮች ለ7ኛው ሥወ መንግሥት በርካታ ተጨማሪ ስሞች (እስከ 70 ፈርዖኖች ድረስ) አስገብተዋል። ከነዚህም ሁሉ አንዱ ስም ብቻ (የነፈርካሬ ነቢ) ኅልውና በሥነ ቅርስ ተረጋግጧል። ስለዚህ ብዙ ሊቃውንት 7ኛው ሥርወ መንግሥት እንደ ኅሣዊ (ታሪካዊ እንዳልሆነ) ይቆጥሩታል።

8ኛው ሥርወ መንግሥት

የማኔጦን 8ኛው ሥርወ መንግሥት እንደገና ብዙ ተጨማሪ ስሞች (በጠቅላላ 27) አሉት። ከነዚህ ሁሉ 3 ብቻ በዕውነት እንደ ነገሡ ይታወቃል። እነርሱም ቃካሬ ኢቢነፈርካውሆር እና ዋጅካሬ ናቸው። ሌሎቹ ስሞች በኋለኛ ዘመን በውሸት እንደ ተፈጠሩ ይታሥባል።

መጀመርያው ጨለማ ዘመን (9ኛው-11ኛው ሥርወ መንግሥታት)

ከጥንታዊው መንግሥት መጨረሻ በኋላ ሥነ ቅርስ ስለሚከተለው ዘመን (2758-2413 ዓክልበ. ግድም) ዝም ይላል። ከዚሁም ዘመን በሕዋላ (2413-2002 ዓክልበ. ግድም) ብዙ አይልም። የመቃብሮች ቁጥር እጅግ በመቀነሱ እንዲህ የሕዝብ ቁጥር መቀነሱ ይታወቃል። ፈርዖኖች እንደገና ሲታዩ፣ ዋና ከተማቸው እንደ ዱሮ በሜንፊስ ሳይሆን አሁን በሄራክሌውፖሊስ ይገኛል። ለታሪክ በእርግጥ የታወቁት ፈርዖኖች ጥቂት ናቸው፤ አከታተላቸውና ዘመኖቻቸው የሚጠራጠር ነው።

11ኛው ሥርወ መንግሥት

10ኛው ሥርወ መንግሥት በሄራክሌውፖሊስ እየገዛ፣ ተወዳዳሪው 11ኛው ሥርወ መንግሥት በጤቤስ ወደ ደቡብ ተመሠረተ። ይሄ ሥርወ መንግሥት በመጨረሻ መላውን ግብጽ ያዘ።

መካከለኛው መንግሥት

12ኛው ሥርወ መንግሥት

ሁለተኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው-17ኛው ሥርወ መንግሥታት)

13ኛው ሥርወ መንግሥት

በ13ኛው ሥርወ መንግሥት ውድቀት 16ኛው ሥርወ መንግሥት በጤቤስ፣ ሌላው «የአቢዶስ ሥርወ መንግሥት» በአቢዶስ ተነሡ።

14ኛው ሥርወ መንግሥት

ከነዓን የደረሱ እረኞችና ነጋዴዎች በአባይ ወንዝ አፍ በስሜን ግብጽ ነጻ መንግሥት መሠረቱ። ይህ ለጊዜው ከ13ኛው ሥርወ መንግሥት ጋር አንድላይ ነበር (1821-1742 ዓክልበ. ግድም)፤ ዘመናቸው ግን እርግጠኛ አይደለም።

15ኛው ሥርወ መንግሥት

ከመርነፍሬ አይ ዘመን ቀጥሎ (1661 ዓክልበ.) ሌሎች ከከነዓን ገብተው አዲስ ተወዳዳሪ መንግሥት በስሜን ግብጽ ተነሣ፤ እሱም ሂክሶስ (ኸካ-ሻሱ ወይም «ውጫገር አለቆች») ይባላል።

16ኛው ሥርወ መንግሥት

የ13ኛው ሥርወ መንግሥት ተከታዮች በጤቤስ ናቸው። በዚህም ዘመን አቢዶስ የራሱን የአቢዶስ ሥርወ መንግሥት እንደ ነበረው ይታሥባል።

የሚከተሉት አጫጭር ዘመናት የገዙት ነገሥታት ቅድም-ተከተል እርግጠኛ አይደለም።

በ1590 ዓክልበ. ግድም የ15ኛው ሥርወ መንግሥት (ሂክሶስ) ፈርዖን አፐፒ ጤበስን ማረከ።

17ኛው ሥርወ መንግሥት

ሂክሶስ ከጤቤስ ከወጡ በኋላ የ16ኛው ሥርወ መንግሥት ተከታዮች በጤቤስ ሆኑ። የገዙት ነገሥታት ቅድም-ተከተል እርግጠኛ አይደለም።

አዲሱ መንግሥት (18ኛው-20ኛው ሥርወ መንግሥታት

18ኛው ሥርወ መንግሥት

  • 1 አሕሞስ 1558-1534 ዓክልበ.
  • 1 አመንሆተፕ 1534-1513 ዓክልበ.
  • 1 ቱትሞስ 1513-1501 ዓክልበ.
  • 2 ቱትሞስ 1501-1487 ዓክልበ.
  • ንግሥት ሃትሸፕሱት 1487-1466 ዓክልበ.
  • 3 ቱትሞስ 1487-1433 ዓክልበ.
  • 2 አመንሆተፕ 1435-1409 ዓክልበ.
  • 4 ቱትሞስ 1409-1399 ዓክልበ.
  • 3 አመንሆተፕ 1399-1361 ዓክልበ.
  • አኸናተን 1361-1344 ዓክልበ.
  • ንግሥት (?) ነፈርነፈርኑአተን 1344-1341 ዓክልበ.
  • ስመንኽካሬ 1341-1340 ዓክልበ.
  • ቱታንኻመን 1340-1331 ዓክልበ.
  • አይ 1331-1327 ዓክልበ.
  • ሆረምኸብ 1327-1300 ዓክልበ.

19ኛው ሥርወ መንግሥት

  • 1 ራምሴስ 1300-1298 ዓክልበ.
  • 1 ሰቲ 1298-1287 ዓክልበ.
  • 2 ራምሴስ 1287-1221 ዓክልበ.
  • መርነፕታህ 1221-1211 ዓክልበ.
  • 2 ሰቲ 1211-1205 ዓክልበ.
  • ሲፕታህ 1205-1199 ዓክልበ.
  • ንግሥት ተዎስረት 1199-1197 ዓክልበ.

20ኛው ሥርወ መንግሥት

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.