የግብጽ ሁለተኛ ማዕከለኛ ዘመን

የግብጽ ሁለተኛ ማእከለኛ ዘመንጥንታዊ ግብጽ ታሪክ ከመካከለኛው መንግስት ቀጥሎና ከአዲሱ መንግሥት በፊት ወይም ከ1819 እስከ 1558 ዓክልበ. ድረስ የነበረው ጊዜ ነበር።

በዚሁ ዘመን ግብጻውያን አገራቸውን ለራሳቸው ብቻ የያዙት ብቻ ሳይሆን ብዙ ሴማዊ ሕዝቦች አብረው ይገኙ ነበር። ከዚህ ዘመን በፊት ወይም በኋላ በመነጻጸር በመዝገቦች ጉድለት ምክንያት ዘመኑ ደግሞ ሁለተኛው የግብጽ ጨለማ ዘመን ተብሏል።

ይህ የ13ኛው ሥርወ መንግሥት፣ የ14ኛው ሥርወ መንግሥት፤ የ15ኛው ሥርወ መንግሥት፤ የ16ኛው ሥርወ መንግሥት፤ የ17ኛው ሥርወ መንግሥትየአቢዶስ ሥርወ መንግሥት ዘመኖች ያጠቀለለ ነበር። ከነዚህም ሁለት ወይም ሦስት ግብጽን በከፊል ያካፈሉባቸው ጊዜዎች ነበሩ። 14ኛውና 15ኛው ሥርወ መንግሥታት ደግሞ ግብጻዊ ሳይሆኑ ሴማዊ (በቋንቋ) ነበሩ።

በመካከለኛው መንግሥት 12ኛው ሥርወ መንግሥት መጨረሻ ንግሥት በሶበክነፈሩ ዘመን በ1821 ዓክልበ. ግድም በስሜን ግብጽ የተገኙት ሴማዊ ነጋዴዎች በራሳቸው ፈርዖን ሥር እንዲሆኑ ፈቀደች። ይህም 14ኛው ሥርወ መንግሥት ይባላል። የሚከተለው ግብጻዊ ንጉሥ ጤቤስን እንጂ መላውን ግብጽ ስላልገዛ 13ኛው ሥርወ መንግሥት ተብሎ ይታወቃል። ከዚሁ ሥርወ መንግሥት አንዱ ፈርዖን ኡሰርካሬ ኸንጀር (1774-66 ዓክልበ.) እራሱ ሴማዊ ስም (ኸንጀር = እሪያ፣ በግዕዝ ሕንዚር) እንዳለው ይታስባል። በ3 ሶበክሆተፕ ዘመን (1741 ዓክልበ.) የሴማውያን መንግሥት እንደ ተሠረዘ፣ ባርዮችም እንደ ሆኑ ይመስላል።

ከዚያው ለጊዜው የ13ኛው ሥርወ መንግሥት ፈርዖኖች መላውን ግብጽ እንደ ገዙ ይመስላል። ከመርነፈሬ አይ ዘመን በኋላ (1661 ዓክልበ.) ግን የግብጽ ኃይል እንደገና ደክሞ የአሞራውያን ሂክሶስ ወገን ወይም 15ኛው ሥርወ መንግስት ያንጊዜ ከከነዓን ወረሩ። የመርነፈሬ አይ ተከታዮች ከጤቤስ ሩቅ አልገዙም ነበር። በ1646 ዓክልበ. ወድቆ እሱም በ16ኛው ሥርወ መንግሥት በጠቤስና ተጨማሪ አቢዶስ መንግሥት ተተካ።

ሂክሶስ በ1596 ዓክልበ. የአቢዶስን መንግሥት አስጨረሱ፤ በ1591 ዓክልበ. ጤቤስንም ይዘው 16ኛውንም ሥ.መ. አስጨረሱ። በ1588 ዓክልበ. ግን አዲስ 17ኛው ሥ.መ. በጤቤስ ተነሣ። ከብዙ ጦርነት በኋላ ፈርዖኑ 1 አሕሞስ በ1558 ዓክልበ. ሂክሶስን በሙሉ አባረራቸው፤ ይህም የግብጽ አዲሱ መንግሥትና 18ኛው ሥርወ መንግሥት መሠረት ይቆጠራል።

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.