የካቲት ፲፭
የካቲት ፲፭፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፷፭ ነኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፶ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፩ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻ ቀናት ይቀራሉ።
ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - ራስ ደስታ ዳምጠውቡታጅራ አካባቢ ላይ በትግራይ ተወላጁ በደጃዝማች ተክሉ መሸሻ ተይዘው በፋሺስት ኢጣልያእጅ ወደቁ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ግብጽ እና ሶርያ የአረብ ሪፑብሊ ኅብረትን (United Arab Republic) መሠረቱ። ይሄ የሁለቱ አገሮች ኅብረት ከሦስት ዓመታት በኋላ ቢፈርስም የግብጽ መጠሪያ ስሟ ሆኖ ለብዙ ዓመታት ቆይቷል።.
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ሎንዶን በሕክምና ላይ የነበሩትን የኢትዮጵያ መንግሥት አልጋ ወራሽ፣ መርድ አዝማች አስፋ ወሰንን ለመጠየቅ መጥተው የነበሩት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በዛሬው ዕለት በባኪንግሀም ቤተ መንግሥት ዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ የ’ሻይ’ ግብዣ አደረጉላቸው።
ልደት
ዋቢ ምንጮች
- (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/1660
- (እንግሊዝኛ) Ibid., FCO 371/1829
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.