የኤሌክትሪክ ፈሳሻዊ ተምሳሌት

በኤሌክትሪክ አስተላላፊ ብረቶች ውስጥ የሚጓዘው ኤሌክትሪክ ጅረት በአይን ስለማይታይ ብዙ ጊዜ ጸባዩን ለማወቅ አስቸጋሪ ይሆናል። የመጀመሪያዎቹ የኤሌክትሪክ ፍሰት ተመራማሪዎች ኤሌክትሪክ ፍሰትን ይረዱት የነበረው በቱቦ ውስጥ በሚፈስ ውሃ ወይም ፈሳሽ ነገር ተምሳሌትነት ነበር። በዚህ ብቻ ሳይበቁ እራሱ ኤሌክትሪክ ፈሳሽ ነገር ነው ይሉ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ያ ግንዛቤ ስህተት መሆኑ የተረጋገጠ ቢሆንም የፈሳሽ ዝውውር አሁን ድረስ ለኤሌክትሪክ ፍሰት ተምሳሌትነት ያገለግላል። በዚህ መንገድ ንጥር (አብስትራክት) የሆኑ የሚመስሉን የኤሌክትሪክ አካላት ና እነሱን አጠናቅሮ የያዘን ዑደት ለመረዳት ያገለግላል። ሆኖም እንደማንኛውም ተምሳሌት (አናሎጂ) ዋናውን ተክተው ሊሰሩ ስለማይችሉ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው።

በፈሳሽ ዑደት (ግራ) እና በኤሌክትሪክ ዑደት (ቀኝ) ያለ ምሥሥል

የኤሌክትሪክ አካላት ተምሳሌቶች

ትንሽ ቱቦ
ሽቦዎች
የኤሌክትሪክ ሽቦ በውሃ በተመላ ቱቦ ይመሰላል። በዚህ ጊዜ ቱቦው ከዳርና ከዳር በክዳን እንደተገጠመ ማሰብ ጥሩ ነው። የሽቦውን አንድ ጫፍ ከኤሌክትሪክ ዑደት ጋር ማያያዝ፣ አንዱን የቱቦ ግጣም በመክፍተ ኬሌላ ቱቦ ጋር በማጋጠም ይመሰላል። ምክናቱም ውሃም ሆኔ ኤሌክትርኩ ስለማይዘዋወሩ የትም አይሄዱምና።
ኤሌክትሪክ እምቅ አቅም
በፈሳሽ ጫና ይመሰላል።
ኤሌክትሪክ እምቅ አቅም ልዩነት (ቮልቴጅ)
በሁለት ነጥቦች መካከል ባለ የጫና ልዩነት ይመሰላል።
ኤሌክትሪክ ቻርጅ
በውሃ ብዛት መጠን ይመሰላል።
ኤሌክትሪክ ጅረት
በስነ ፈሳሽ የፍሰት ይዘት ውድር (ቮልዩም ፍሎው ሬት) ይመሰላል። ማለቱ በየሚፈሰው ውሃ ይዘት መጠን በጊዜ ውስጥ ሲለካ።
ቮልቴጅ ምንጭ
በአንድ ቋሚ ጫና የሚሰራ የውሃ ፓምፕ
ጅረት ምንጭ
ምንጌዜም በቋሚ ፍጥነት ውሃ የሚገፋ ፓምፕ (ፓዚቲቭ ዲስፕሌስመንት ፓምፕ)
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.