የአዲስ አበባ ከንቲባ

ከንቲባ፦ ላንተ ይግባ፤ ማዕረጉ ከሊጋባ በታች የሆነ ዋና የራስ ከተማ ሹም፤ ዳኛ፤ገዥ፤ የከተማው ቀረጥና የዳኝነቱ ገንዘብ አንተ ዘንድ ይግባ (ይባእ ኀቤከ) ማለት ነው። ይህ ስም ጥንት ለባላባቶች፣ ለታላላቆችና አገረ ገዦች ስለተሰጠ እስከ ዛሬ ድረስ የሀሳብ ባላባት ከንቲባ ይባላል።

(ደስታ ተክለወልድ ዐዲስ የአማርኛ መዝገበ ቃላት፡ ፷፪)

ዝርዝር

አዲስ አበባ ከተማ ከ፲፱፻፩ እስከ ፲፱፻፺፰ ዓ.ም ድረስ ፳፰ ከንቲባዎች መፈራረቃቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።[1] እነዚህም፦

ተራ ቁጥር ስም ያገለገሉበት ዘመን (ዓ.ም.)
ቢትወደድ ወልደ ፃዲቅ ከ፲፱፻፩ እስከ ፲፱፻፰
ቢትወደድ ኃይለ ጊዮርጊስ ፲፱፻፱
ደጃዝማች ይገዙ በሀብቴ ፲፱፻፲
ወሰኔ ዘአማኔል ፲፱፻፲
ደጃዝማች ማተቤ ፲፱፻፲
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ፲፱፻፲ እስከ ፲፱፻፲፬
ነሲቡ ዘአማኔል ከ፲፱፻፲፬ እስከ ፲፱፻፳፫
ራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው ከ፲፱፻፳፬ እስከ ፲፱፻፳፮
ደጃዝማች ቢትወደድ ጤና ጋሻው ከ፲፱፻፳፮ እስከ ፲፱፻፳፰
ራስ አበበ አረጋይ ፲፱፻፴፫
፲፩ ደጃዝማች ታከለ ወልደሐዋርያት ፲፱፻፴፬ ?
፲፪ ደጃዝማች ከበደ ተሰማ ከ፲፱፻፴፬ እስከ ፲፱፻፴፰ ?
፲፫ ራስ መስፍን ስለሺ ፲፱፻፴፫ ?
፲፬ ፊታውራሪ ደምሴ ወልደአማኑኤል ከ፲፱፻፴፰ እስከ ፲፱፻፵፯
፲፭ ብላቴን ጌታ ዘውዴ በላይነህ ለአንድ ዓመት ብቻ
፲፮ ብላታ ትርፌ ሹምዬ ፲፱፻፵፰
፲፯ ደጃዝማች ዶ/ር ዘውዴ ገብረሥላሴ ከ፲፱፻፶ እስከ ፲፱፻፶፪
፲፰ ቢትወደድ ዘውዴ ገብረሕይወት ለ፫ ዓመታት
፲፱ ዶ/ር ኃይለጊዮርጊስ ወርቅነህ
ኤንጂነር መኮንን ሙላት ከ፲፱፻፷፮ ጀምሮ ለ፬ ዓመታት
፳፩ ዶ/ር ዓለሙ አበበ ከ፲፱፻፸ እስከ ፲፱፻፸፫
፳፪ ኤንጂነር ዘውዴ ተክሉ ከ፲፱፻፸፫
፳፫ አቶ ግዛው ንጉሴ ከ፲፱፻፹፩ እስከ ፲፱፻፹፫
፳፬ አቶ ሙሉዓለም አበበ ከ፲፱፻፹፫ እስከ ፲፱፻፹፭
፳፭ አቶ ተፈራ ዋልዋ ከ፲፱፻፹፫ እስከ ፲፱፻፺
፳፮ አቶ አሊ አብዶ ከ፲፱፻፺ እስከ ፲፱፻፺፭
፳፯ አቶ አርከበ እቁባይ ከጥር ፲፮ ቀን ፲፱፻፺፭ እስከ ግንቦት ፩ ቀን ፲፱፻፺፰ ዓ.ም.[2]
፳፰ አቶ ብርሃነ ዴሬሳ (ተግባራዊ) ከግንቦት ፩ ቀን ፲፱፻፺፰ እስከ ግንቦት ፲፪ ቀን ፳፻ ዓ.ም.[2]
፳፱ አቶ ኩማ ደመቅሳ
አቶ ድሪባ ኩማ

ማመዛገቢያ

  1. አ.አ. ሚሌኒየም ጽ/ቤት አዲስ አበባ ባለፈውና በአዲሱ ሚሌኒየም ገጽ 13-19
  2. (እንግሊዝኛ) Ethiopia Regions
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.