የንቅያ ጸሎተ ሃይማኖት

የንቅያ ጸሎተ ሃይማኖት በአብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት የሚቀበል የክርስትና እምነት መግለጫ ነው።

በኒቅያ የሃይማኖትን ፀሎት የደነገጉ ቅዱሳን ሊቃነ አበው
የንቅያ ጉባዔ ተሳታፊዎች በመዐከል ፃድቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጥንጢኖስ
የክርስትና እምነት የተመሠረተበት ጉባዔ
ሰብሳቢ ፃድቁ ንጉሥ ቆስጥንጢኖስ
የተወሰነበት ቀን ፫የ፸፪ ዓ.ም
የተሰበሰቡት ሊቃነ አበው ብዛት ፫የ፲፰ ሊቃነ አበው
ቦታው በንቅያ ቁስጥንጥኒያ
የሚከበርበት ቀን ኅዳር ፱ ቀን በመላው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንዲሁም በአብ በወልድ በመንፈስቅዱስ እምንት ውስጥ ባሉ ሃይማኖቶች

እንዲያውም የዛሬው ጸሎት ከኒቅያ ጉባኤ በኋላ፣ በቁስጥንጥንያ ጉባኤ የተዘጋጀው ነው። ሁለተኛው ጉባኤ አንዳንድ ቃላት በተለይም ስለ መንፈስ ቅዱስ በይበልጥ የሚገልጽ ቋንቋ ተጨመረ። በመጀመርያውም እትም፣ መጨረሻው ዓረፍተ ነገር ሀረ ጤቆች ይወገዙ ይል ነበር፤ በዚህ ፈንታ አዲሱ ጸሎተ ሃይማኖት የጥምቀትየሙታን ትንሳኤና ዘላለም ሕይወት እምነቶች ይጠቅሳል።

ከ372 ዓም ጀምሮ እስካሁን በምንም ሳይቀየር፣ ሮማን ካቶሊክፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያን ሁሉ በሙሉ ይቀበላሉ። ሞርሞኖች ወይም የይሆዋ ምሥክሮች ግን ሥላሴን የማይቀበሉ እምነቶች ናቸው።

የሃይማኖት ጸሎት (የተሻለው 372 ዓ.ም. ቁስጥንጥንያ እንደ ተዘጋጀ)

ኹሉን በያዘ፣ ሰማይንና ምድርን፥ የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ፡ አንድ አምላክ በሚኾን፡ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን።

ዓለም ሳይፈጠር፡ ከእርሱ ጋራ በነበረ፥ አንድ የአብ ልጅ፥ አንድ ጌታ በሚኾን፡ በእግዚአብሔር ወልድም እናምናለን። እርሱም፡ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፥ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ፥ የተወለደ እንጂ፡ ያልተፈጠረ፣ በመለኮቱ፡ ከአብ ጋራ የሚተካከል፣ ኹሉ፡ በእርሱ የኾነው፡ ኢየሱስ ክርስቶስ| ነው። በሰማይ ካለው፣ በምድርም ካለው፡ ያለእርሱ፡ ምንም ምን፡ የኾነ የለም።

ስለእኛ ስለሰዎች፥ እኛን ለማዳን፡ ከሰማይ ወረደ፤ በመንፈስ ቅዱስ ግብር፡ ከቅድስት ድንግል ማርያም፡ ከሥጋዋ፡ ሥጋ፥ ከነፍሷ፡ ነፍስ ነሥቶ፡ ፍጹም ሰውን ኾነ። በጴንጤናዊው ጲላጦስ ዘመን፡ ስለእኛ፡ መከራን ተቀበለ። ተሰቀለ። ሞተ። ተቀበረ። በሦስተኛውም ቀን፡ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ። በክብር፥ በምስጋና፡ ወደሰማይ ዐረገ። በአባቱም ቀኝ፡ በዙፋኑ ተቀመጠ። ዳግመኛም፡ በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ፡ በምስጋና ይመለሳል። ለመንግሥቱ፡ ፍጻሜ የለውም።

በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም እናምናለን። እርሱም፡ ሕይወትን የሚሰጥ፣ ከአብ የሠረፀና በነቢያት ዐድሮ የተናገረው፥ በሓዋርያት ላይ የወረደውና በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት፡ ዓለሙን፡ በጸጋው የሞላው፡ ቅዱሱ የእውነት መንፈስ ነው። ለእርሱም፡ ከአብና ከወልድ ጋራ፡ በአንድነት እንሰግድለታለን፤ እናመሰግነዋለንም። በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን። ኃጢኣት በሚሠረይባት፡ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን።

የሙታን ትንሣኤ ተስፋ እናደርጋለን፥ በዘለዓለምም ሕይወት እናምናለን። ለዘለዓለሙ፤ አሜን።

በመጀመርያው ንቅያ ጉባኤ በ317 ዓ.ም. እንደ ተጻፈ

ኹሉን በያዘ፣ የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ፡ አንድ አምላክ በሚኾን፡ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን።

ከእርሱ ጋራ በነበረ፥ የአብ ልጅ፥ አንድ ጌታ በሚኾን፡ በእግዚአብሔር ወልድም እናምናለን። እርሱም፡ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፥ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ፥ የተወለደ እንጂ፡ ያልተፈጠረ፣ በመለኮቱ፡ ከአብ ጋራ የሚተካከል፣ ኹሉ፡ በእርሱ የኾነው፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በሰማይ ካለው፣ በምድርም ካለው፡ ያለእርሱ፡ ምንም ምን፡ የኾነ የለም።

ስለእኛ ስለሰዎች፥ እኛን ለማዳን፡ ወረደ፤ ነፍስ ነሥቶ፡ ፍጹም ሰውን ኾነ። መከራን ተቀበለ። በሦስተኛውም ቀን፡ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ። ወደሰማይ ዐረገ። ዳግመኛም፡ በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ፡ ይመለሳል።

በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም እናምናለን።

ነገር ግን፣ «ያልተገኘበት ዘመን ነበር» እና «ሳይፈጠር አልነበረም» እና «ከአንዳችም ተፈጠረ»፣ ወይም «ከሌላ ባሕርይ ነው» ወይም «የእግዚአብሔር ወልድ ይፈጠራል» ወይም «የሚለወጥ ነው» የሚሉት፦ በቅድሥት ካቶሊክ እና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ይወገዙ።

ዋቢ ምንጭ

    This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.