የቴቭኒን እርግጥ

የቴቭኒን እርግጥ የተወሳሰበን የኤሌክትሪክ ዑእት ወደ ቀላል ተመጣጣኝ ዑደት የምንልወጥበት መንገድ ነው። በእርግጡ መሰረት ብዙ ባትሪየኤሌክትሪክ ጅረት ምንጮች እና ሁለት ጫፍ ያላቸው ተቃዋሚዎች (ሬዚዝተርስ) ያለውን የኤሌክትሪክ ዑደት በአንድ የቮልቴጅ አመንጭና ከርሱ ጋር በተቀጠለ አንድ ተቃዋሚ ዑደት ሊተካ ይችላል ነው። ስለሆነም ውስብስብ የሚመስልን አንድ ዑደት ወደ ቀላል ዑደት በቴቭኒን እርጉጥ ማሻገር ይቻላል።

የተወሳሰበው የግራው የኤሌክትሪክ ዑደት በቴቭኒን እርጉጥ መሰረት ተቃሎ በተመጣጣኙ የቀኝ ዑደት ይተካል ።
ሊኒያር መረብ ትንታኔ
አባላት

መጠነ እንቅፋት(ሬዚስታንስ) Resistanceካፓሲታንስ capacitanceኢንደክታንስ Inductance

አካላት

ቅጥልና ትይዩ ዑደቶች

ተመጣጣኝ ኢምፔዳንስ

ተመጣጣኝ እርግጦች የኤሌክትሪክ መረብ እርግጦች

መረብ መተንተኛ ዘዴዎች

ሁለት ጫፍ መረብ ትንታኔ

z-ፓራሜትሮችy-ፓራሜትሮችh-ፓራሜትሮችg-ፓራሜትሮችS-ፓራሜትሮች

የቴቭኒን እርግጥ መጀመሪያ ይተደረሰበት በኸርማን ሄልሞዝ በ1845 ቢሆንም ከንደገና በ1875 በፈረንሳዩ ላየን ቴቭኒን ከንደገና ስለተደረሰበት በዚህ በሁለተኛው ሳይንቲስት ስም እስካሁን ይጠራል።

የቴቭኒን እኩያ

ብዙ የተወሳሰበ አንድ ዑደት በተቃዋሚና ከርሱ ጋር በቀጠለ የቮልቴጅ ምንጭ ቀላል ዑደት ሲተካ፣ ይህ አዲሱ ዑደት የቴቭኒን እኩያ ይባላል። ማለት አንድ ቴሌቭዥን፣ ውስጡ ያለውን ውጥንቅጡ የወጣ ዑደት በአንዲት ተቃዋሚ እና ባትሪ እንደመተካት ማለት ነው (ለምሳሌ ነው እንጂ ይሄ በተግባር አይሰራም ምክንያቱም ቴሌቭዥን በውስጡ ዳዮድ እና መሰል ሊኒያር ያልሆኑ የኤሌክትሪክ አካላት አሉት፣ የቴቭኒን እርግጥ ደግሞ የሚሰራ ለሊኒያር የኤሌክትሪክ ዑደት ብቻ ነው)።

የቴቭኒን እኩያ አቀማመር

  1. የዑደቱ ጭነት ይወገዳል። ስለሆነም ዑደቱ በጭነቱ ቦታ ክፍት ዑደት ይፈጥራል ( ማለት በA እና B ጫፎች ላይ የሚገኝ ማናቸውም ጭነት ይወገዳል)
  2. በዚህ በጭነቱ ምትክ በተሰራ ክፍት ዑደት ላይ ያለው ወጭው ቮልቴጅ VAB ይሰላል። ይህ እንዲህ የቴቭኒን ቮልቴጅ VTh የሚሰኘው ነው።
  3. ከዚያም የጭነቱን ማያያዣ ጫፎች በቀጥታ በሽቦ በማያያዝ በዚህ ሽቦ ውስጥ የሚጓዘውን የኤሌክትሪክ ጅረት IAB መለካት (ማስላት)። የቴቭኒን ተቃዋሚ እንግዲህ የቴቭኒንን ቮልቴጅ ለቴቭኒን ጅረት በማካፈል ይሰላል።

3ኛውን ደረጃ በሌላ መንገድም ማግኘት ይቻላል።

3ሀ. ሁሉንም የቮልቴጅ ምንጮች በቀጥታ ሽቦ መተካት። የኤሌክትሪክ ጅረት ምንጮችን ደግሞ በክፍት ዑደት መተካት።
3ለ. በጫፍ A እና B መካከል ያለውን ተቃውሞ ማስላት። ይሄውም የቴቭኒን ተቃዋሚ RTh ይሰኛል።

ምሳሌ

Step 0: ውስብስብ ዑደት
Step 1: እኩያ ወጭ ቮልቴጅ ሲሰላ
Step 2: እኩያ ተቃውሞ ሲሰላ
Step 3: ለተወሳሰበው የመጀመሪያ ዑደት አጠቃላዩ እኩያ ዑደት

ከላይ የተሰጠው ዑደት እኩያ በሂሳብ ቋንቋ እንዲህ ይተረጎማል

( R1 እዚህ ስሌት ላይ ፋይዳ የለውም። ለዚህ ምክንያቱ የዑደቱ በጫፍ A እና B መካከል የተፈጠረው ክፍት ዑደት ነው። ማለት በሁለቱ ጫፎች መካከል የኤሌክትሪክ ጅረት መንቀሳቀስ ስለማይችል በ R1 ውስጥ ምንም ጅረት የለም ስለሆነም ምንም ቮልቴጅ የለም (የኦም ህግ) )

እኩያ ተቃዋሚው ደግሞ በሂሳብ እንዲህ ይተረጎማል:

የቴቭኒን እርግጥ የስራ ወሰን

  • የቴቭኒን እርግጥ እሚሰራ ለሊኒያር ዑደት ብቻ ነው። ስለሆነም በተግባር ሲውል ጥንቃቄ ያሻዋል ምክንያቱም ብዙ ዑደቶች ሊኒያረ ከሚሆኑበት የማይሆኑበት ሁኔታ ይበዛልና።
  • የቴቭኒን እኩያ ጅረት-ቮልቴጅ ጠባይ ከዑደቱ ጭነት አንጻር ብቻ ነው ስሜት የሚሰጠው።
  • የቴቭኒን እኩያ ኃይል ፍጆታ ከዋናው ዑደት ኃይል ፍጆታ ጋር ሁልጊዜ አንድ አይደለም።


ተጨማሪ ንባብ (እንግሊዝኛ)

This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.