የቴቭኒን እርግጥ
የቴቭኒን እርግጥ የተወሳሰበን የኤሌክትሪክ ዑእት ወደ ቀላል ተመጣጣኝ ዑደት የምንልወጥበት መንገድ ነው። በእርግጡ መሰረት ብዙ ባትሪ ፣ የኤሌክትሪክ ጅረት ምንጮች እና ሁለት ጫፍ ያላቸው ተቃዋሚዎች (ሬዚዝተርስ) ያለውን የኤሌክትሪክ ዑደት በአንድ የቮልቴጅ አመንጭና ከርሱ ጋር በተቀጠለ አንድ ተቃዋሚ ዑደት ሊተካ ይችላል ነው። ስለሆነም ውስብስብ የሚመስልን አንድ ዑደት ወደ ቀላል ዑደት በቴቭኒን እርጉጥ ማሻገር ይቻላል።
ሊኒያር መረብ ትንታኔ | |
---|---|
አባላት | |
| |
አካላት | |
| |
ቅጥልና ትይዩ ዑደቶች | |
| |
ተመጣጣኝ ኢምፔዳንስ | |
| |
ተመጣጣኝ እርግጦች | የኤሌክትሪክ መረብ እርግጦች |
|
|
መረብ መተንተኛ ዘዴዎች | |
| |
ሁለት ጫፍ መረብ ትንታኔ | |
| |
የቴቭኒን እርግጥ መጀመሪያ ይተደረሰበት በኸርማን ሄልሞዝ በ1845 ቢሆንም ከንደገና በ1875 በፈረንሳዩ ላየን ቴቭኒን ከንደገና ስለተደረሰበት በዚህ በሁለተኛው ሳይንቲስት ስም እስካሁን ይጠራል።
የቴቭኒን እኩያ
ብዙ የተወሳሰበ አንድ ዑደት በተቃዋሚና ከርሱ ጋር በቀጠለ የቮልቴጅ ምንጭ ቀላል ዑደት ሲተካ፣ ይህ አዲሱ ዑደት የቴቭኒን እኩያ ይባላል። ማለት አንድ ቴሌቭዥን፣ ውስጡ ያለውን ውጥንቅጡ የወጣ ዑደት በአንዲት ተቃዋሚ እና ባትሪ እንደመተካት ማለት ነው (ለምሳሌ ነው እንጂ ይሄ በተግባር አይሰራም ምክንያቱም ቴሌቭዥን በውስጡ ዳዮድ እና መሰል ሊኒያር ያልሆኑ የኤሌክትሪክ አካላት አሉት፣ የቴቭኒን እርግጥ ደግሞ የሚሰራ ለሊኒያር የኤሌክትሪክ ዑደት ብቻ ነው)።
የቴቭኒን እኩያ አቀማመር
- የዑደቱ ጭነት ይወገዳል። ስለሆነም ዑደቱ በጭነቱ ቦታ ክፍት ዑደት ይፈጥራል ( ማለት በA እና B ጫፎች ላይ የሚገኝ ማናቸውም ጭነት ይወገዳል)
- በዚህ በጭነቱ ምትክ በተሰራ ክፍት ዑደት ላይ ያለው ወጭው ቮልቴጅ VAB ይሰላል። ይህ እንዲህ የቴቭኒን ቮልቴጅ VTh የሚሰኘው ነው።
- ከዚያም የጭነቱን ማያያዣ ጫፎች በቀጥታ በሽቦ በማያያዝ በዚህ ሽቦ ውስጥ የሚጓዘውን የኤሌክትሪክ ጅረት IAB መለካት (ማስላት)። የቴቭኒን ተቃዋሚ እንግዲህ የቴቭኒንን ቮልቴጅ ለቴቭኒን ጅረት በማካፈል ይሰላል።
3ኛውን ደረጃ በሌላ መንገድም ማግኘት ይቻላል።
- 3ሀ. ሁሉንም የቮልቴጅ ምንጮች በቀጥታ ሽቦ መተካት። የኤሌክትሪክ ጅረት ምንጮችን ደግሞ በክፍት ዑደት መተካት።
- 3ለ. በጫፍ A እና B መካከል ያለውን ተቃውሞ ማስላት። ይሄውም የቴቭኒን ተቃዋሚ RTh ይሰኛል።
ምሳሌ
ከላይ የተሰጠው ዑደት እኩያ በሂሳብ ቋንቋ እንዲህ ይተረጎማል
( R1 እዚህ ስሌት ላይ ፋይዳ የለውም። ለዚህ ምክንያቱ የዑደቱ በጫፍ A እና B መካከል የተፈጠረው ክፍት ዑደት ነው። ማለት በሁለቱ ጫፎች መካከል የኤሌክትሪክ ጅረት መንቀሳቀስ ስለማይችል በ R1 ውስጥ ምንም ጅረት የለም ስለሆነም ምንም ቮልቴጅ የለም (የኦም ህግ) )
እኩያ ተቃዋሚው ደግሞ በሂሳብ እንዲህ ይተረጎማል:
የቴቭኒን እርግጥ የስራ ወሰን
- የቴቭኒን እርግጥ እሚሰራ ለሊኒያር ዑደት ብቻ ነው። ስለሆነም በተግባር ሲውል ጥንቃቄ ያሻዋል ምክንያቱም ብዙ ዑደቶች ሊኒያረ ከሚሆኑበት የማይሆኑበት ሁኔታ ይበዛልና።
- የቴቭኒን እኩያ ጅረት-ቮልቴጅ ጠባይ ከዑደቱ ጭነት አንጻር ብቻ ነው ስሜት የሚሰጠው።
- የቴቭኒን እኩያ ኃይል ፍጆታ ከዋናው ዑደት ኃይል ፍጆታ ጋር ሁልጊዜ አንድ አይደለም።
ተጨማሪ ንባብ (እንግሊዝኛ)
- የተመጣጣኝ ዑደት ጽንሰ ሃሳብ አመሰራረት (እንግሊዝኛ) Archived ሴፕቴምበር 27, 2007 at the Wayback Machine
- ቴቭንን እርግጥ
- ECE 209: ዑደቶች እንደ LTI ስርዓት —