የብሪታንያ መንግሥት
የብሪታንያ መንግሥት (British Empire) ኢንግላንድና ስኮትላንድ በ1699 ዓም እንደ ታላቅ ብሪታንያ ከተዋሐዱ ጀምሮ ከሌሎች ባህር ማዶ ጥገኛ ግዛቶች ጭምር ማለት ነው።
ከ1699 ዓም አስቀድሞ የኢንግላንድ መንግሥት በአሜሪካ በአትላንቲክ ውቅያኖስ አጠገብ፣ እንዲሁም በካሪቢያን ባህር ዙሪያ አንዳንድ ቅኝ አገራት መሠርተው ነበር። በ1775 ዓም ከአሜሪካዊ አብዮት ቀጥሎ 13ቱ ቅኝ አገሮች ተነቅለው የራሳቸው አገር (ዩናይትድ ስቴትስ) ሆኑ። ካናዳ ግን ለዩናይትድ ኪንግደም ግዛት ሆና ቀረች።
የብሪታንያ ፪ኛ መንግሥት የተባለው ከዚህ በኋላ በተለይ በእስያ፣ በአፍሪካና በአውስትራሊያ ይስፋፋ ጀመር። የግዛቱም ጫፍ በ1912 ዓም ያህል ተከሰተ። ከ2ኛ ዓለማዊ ጦርነት ቀጥሎ ብዙዎቹ ቅኝ አገሮቿ ነጻነታቸውን በሰላማዊነት አገኙ። በአሁኑ ሰዓት ለዩናይትድ ኪንግደም 14 ጥቃቅን ባህር ማዶ ግዛቶች ብቻ ቀርተዋል። በተጨማሪ የዩናይትድ ኪንግደም ንግሥት ዳግማዊት ኤልሳቤጥ እስካሁን የሌሎች 15 አገራት ንግሥት ሆነው ቀርተዋል።
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.