የባሕር ምድር ሥርወ መንግሥት

የባሕር ምድር ሥርወ መንግሥት በቀድሞ ሱመር (ደቡብ መስጴጦምያ ወይም ከላውዴዎን) ከባቢሎኒያ መንግሥት ተለይቶ የተነሣ መንግሥት ነበር።


በ1645 ዓክልበ. አካባቢ የኢሲን ከንቲባ ኢሉማ-ኢሊሃሙራቢ ልጅ በባቢሎን ንጉሥ ሳምሱ-ኢሉና ላይ በዓመጽ ተነሣና ሥርወ መንግሥቱን መሠረተ። ነገሥታት ሱመራዊ ስሞች ቢወስዱም፣ ያንጊዜ መደበኛ ቋንቋ አካድኛ እንደ ሆነ ይመስላል።

በባሕር ምድር ሥርወ መንግሥት ውስጥ የሚከተሉት ነገሥታት ከአንዳንድ ዝርዝር ጽላት ታውቀዋል። አንዱም ጽላት የነገሡበት ዘመን አመታት ቁጥር ቢሰጥም፣ የነዚህ ድምር ግን 368 ዓመታት ሲሆን በእውነት የቆዩበት ዓመት ከ1645-1463 ዓክልበ ወይም 182 ዓመታት ብቻ ይመስላል።

#ጽላት ሀ[1]ጽላት ለ[2]ዘመን በጽላት ሀ ዘንድበዘመኑ በባቢሎን የነገሱ
1ኢሊማኢሉማ-ኢሊ60 ዓመትሳምሱ-ኢሉና (1662-1624 ዓክልበ)፣ አቢ-ኤሹሕ (`1624-1596 ዓክልበ.)
2ኢቲሊኢቲ-ኢሊ-ኒቢ56 ዓመት
3ዳምቂሊዳምቂ-ኢሊሹ36 ዓመትአሚ-ዲታና መጨረሻ ዓመት ይጠቀሳል (1559 ዓክልበ.)
4እሽኪእሽኪባል15 ዓመት
5ሹሺ (ወንድሙ)ሹሺ24 ዓመት
6ጉልኪ…ጉልኪሻር55 ዓመትሳምሱ-ዲታና (1538-1507 ዓክልበ.)
7ፐሽጋልፐሽጋልዳራመሽ (ልጁ)50 ዓመት
8ዓዳራአዳራጋላማ (የጉልኪሻር ልጅ)28 ዓመትካሣውያን
9ኤኩሩልአኩርዱዓና26 ዓመት
10መላማመላምኩርኩራ7 ዓመት
11ኤዓጋኤዓ-ጋሚል9 ዓመትበካሣውያን ንጉሥ ኡላም-ቡርያሽ በ1463 ዓክልበ. ግድም ተባረረ

አንድ ሌላ ጽላት A-117 እንደ ጽላት «ለ» ያላቸውን ስሞች ከአሦራዊ ነገሥታት ዘመናት ጋራ ለማስማማት ይሞክራል፣ ሆኖም በትክክል አልተስማሙም። ከ1675 እስከ 1561 ዓክልበ ያህል ድረስ የገዙት አሦር ነገሥታት የዘመን ባልንጀሮቻቸው ቢላቸውም፣ ይህ ልክ እንደማይሆን ሊታወቅ ይቻላል።

ከዚህ በላይ ስለነዚህ ነገሥታት የምናውቀው ጥቂት ብቻ ነው።

  • ኢሉማ-ኢሊ ሳምሱ-ኢሉናን እንሳሸነፈው ይተረካል፣ ዓመት ስሞቹም በኒፑር ተገኝተው ኒፑርን እንደ ያዘ ይታስባል። የሳምሱ-ኢሉና ተከታይ አቢ-ኤሹሕ ደግሞ ኢሉማ-ኢሊን ለማሸነፍ ሲሞክር ጠግሮስ ወንዝን ገደበ፤ ይህ ግን ስኬታም አሆነለትም።
  • ዳምቂ-ኢሊሹ፦ የአሚ-ዲታና መጨረሻ አመት ስም «የዳምቂ-ኢሊሹ ኃያላት የሠሩት ግድግዳ ያፈረሰበት አመት» ተባለ። የዳምቂ-ኢሊሹ ስም የቀድሞ ኢሲን መጨረሻ ንጉስ ዳሚቅ-ኢሊሹን (1731-1709) ያሳስባል።
  • ጉልኪሻር ከባቢሎን መጨረሻ ንጉሥ ሳምሱ-ዲታና ጋር እንደ ታገለ በአንድ ታሪክ ጽላት ተቀረጸ። የብርጭቆ አሠራር የሚገልጽ አንድ ጽላት «ጉልኪሻር ዘውድ ከተጫነበት ዓመት በኋላ በሆነው ዓመት» ተጽፎ ተገኝቷል። ከብዙ መቶ ዘመናት በኋላ በነገሠው በኤንሊል-ናዲን-አፕሊ ዘመን (1113-1109 ዓክልበ.) በተጻፈ ሰነድ ዘንድ፣ ጉልኪሻር የመቅደስን ርስት ከ696 ዓመታት በፊት እንደ ወሰነ ይጠቅሳል፤ በውነት ግን 400 ያህል ዓመታት እንዳለፉ ይሆናል።
  • ፐሽጋልዳራመሽ እና አዳራጋላማ የጉልኪሻር ልጆች ይባላሉ። ብዙ ሰነዶች ከዘመኖቻቸው ተገኝተዋል። በአንድ ሰነድ በፐሽጋልዳራመሽ ፯ኛው ዓመት ወንድሙ አዳራጋላማ ደግሞ የጋርዮሽ ንጉሥ ይባላል። ከሌላ ሰነድ አዳራጋላማ ብቻ ንጉሥ የሆነው ከፐሽጋልዳራመሽ 29ኛው አመት በኋላ ነበር። ስለዚህ ወንድሞቹ ለ22 አመት ያህል የጋርዮሽ ዘመን ስለነበራቸው፣ ብዙ የሥርወ መንግሥቱ ነገሥታት ከተከታዮቻቸው ጋራ ረጅም ጋርዮሽ ዘመናት እንዳገኙ ይቻላል። አዳራጋላማ በካሣውያንና በኤላማውያን ላይ ድል እንዳደረገ ይታወቃል።
  • ኤዓ-ጋሚል በካሣውያን ንጉሥ ኡላም-ቡርያሽ በ1463 ዓክልበ. ግድም ወደ ኤላም እንደ ተባረረ ይዘገባል።
  1. Babylonian King List A, BM 33332,
  2. Babylonian King List B, BM 38122.
This article is issued from Wikipedia. The text is licensed under Creative Commons - Attribution - Sharealike. Additional terms may apply for the media files.